Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 20:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ስለዚህ እግዚአብሔር የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፤ ሁሉም ለእርሱ በሕይወት ይኖራሉ።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ሁሉም ለርሱ ሕያዋን ስለ ሆኑ፣ እርሱ የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አይደለም።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ሁሉም ለእርሱ ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 እን​ኪ​ያስ የሕ​ያ​ዋን አም​ላክ እንጂ የሙ​ታን አም​ላክ አይ​ደ​ለም፤ ሁሉም በእ​ርሱ ዘንድ ሕያ​ዋን ናቸ​ውና።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ሁሉ ለእርሱ ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም።

See the chapter Copy




ሉቃስ 20:38
18 Cross References  

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ስለ ሆንኩ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ፤


እርሱ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሞተው በደካማነት ቢሆንም አሁን በእግዚአብሔር ኀይል በሕይወት ይኖራል፤ እኛም ከእርሱ ጋር ደካሞች ሆነናል፤ ከእናንተ ጋር ባለን ግንኙነት ግን ከእርሱ ጋር በእግዚአብሔር ኀይል እንኖራለን።


የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖቶች ጋር ምን ስምምነት አለው? እግዚአብሔርም፦ “መኖሪያዬን በሕዝቤ መካከል አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር እኖራለሁ፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ” ብሎ እንደ ተናገረው እኛ እያንዳንዳችን የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን።


ከዚህ በኋላ መልአኩ ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብሩህ መስተዋት ጥርት ያለውን የሕይወት ውሃ ወንዝ አሳየኝ፤


አሁን ግን የሚበልጠውን፥ በሰማይ ያለውን አገር ይናፍቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማን ስላዘጋጀላቸው “አምላካችን” ብለው ቢጠሩት አያሳፍረውም።


ሕያው አብ እንደ ላከኝና እኔም በእርሱ ሕያው እንደ ሆንኩ እንዲሁም ሥጋዬን የሚበላ ሁሉ በእኔ ሕያው ይሆናል።


እርሱም ያለው እንዲህ ነው፦ ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብ አምላክ ነኝ፤’ ስለዚህ እግዚአብሔር የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም።”


ስለዚህ እግዚአብሔር የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፤ እናንተ ግን እጅግ ትሳሳታላችሁ።”


ከሕግ መምህራንም አንዳንዶቹ “መምህር ሆይ! መልካም ተናገርክ!” አሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements