Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 19:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ጠላቶችሽ በዙሪያሽ ዐጥር ዐጥረውና ከበው፥ በዚህም በዚያም አንቺን የሚያስጨንቁበት ቀን ይመጣል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ጠላቶችሽ ዙሪያሽን ቅጥር ሠርተው፣ ከየአቅጣጫውም ከብበው አንቺን የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣልና፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ጠላቶችሽም በዙርያሽ ቅጥር የሚሠሩበት፥ አንቺን የሚከቡበትና ከሁሉም አቅጣጫ የሚያስጨንቁብት ቀኖች ይመጣሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ጠላ​ቶ​ችሽ አን​ቺን የሚ​ከ​ቡ​በት ቀን ይመ​ጣል፤ ይከ​ት​ሙ​ብ​ሻል፤ ያስ​ጨ​ን​ቁ​ሻ​ልም፤ በአ​ራቱ ማዕ​ዘ​ንም ከብ​በው ይይ​ዙ​ሻል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ወራት ይመጣብሻልና፥ ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል ይከቡሻልም በየበኵሉም ያስጨንቁሻል፤

See the chapter Copy




ሉቃስ 19:43
15 Cross References  

በዋናይቱ ምድር ባሉት መንደሮች ነዋሪ የሆኑ ሕዝብ ሁሉ በጦርነት ያልቃሉ፤ እናንተን የሚከላከልበት ምሽግ ይሠራል። ጠላትም እስከ ቅጽሮችሽ ጫፍ ዐፈር ይደለድላል፤ በጋሻም ብዛት እየተከላከለ ያጠቃችኋል።


ልክ እንደ አንድ ከተማ አስመስለህ በጡቡ ላይ አደጋ ለመጣል ተዘጋጅ፤ እስከ ጫፍ ድረስ የዐፈር ቊልልና መወጣጫ ሠርተህ ጡቡን በጠላት ወታደር እንደሚከበብ አስመስለህ ክበባት። በሁሉም አቅጣጫ የእንጨት ምሰሶ ሠርተህ የከተማይቱን የቅጥር በር የምታፈርስ አስመስል።


“ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ አሦራውያን ንጉሥ የተናገረውም ቃል ይህ ነው፤ ‘ሰናክሬም ወደዚህች ከተማ ፈጽሞ አይገባባትም፤ አንድ ፍላጻ እንኳ አይወረውርባትም፤ ጋሻ ያነገበ ወታደርም ወደ እርስዋ አይቀርብም፤ በዐፈር ቊልልም አትከበብም።


በዚህ ጊዜ ንጉሡ ተቈጣና ወታደሮቹን ልኮ እነዚያን ገዳዮች አስገደለ፤ ከተማቸውንም በእሳት እንዲያቃጥሉ አደረገ፤


ጥቂት ሕዝብ የሚኖርባት አንዲት ትንሽ ከተማ ነበረች፤ አንድ ኀይለኛ ንጉሥ አደጋ ሊጥልባት ተነሣ፤ ትልቅ ምሽግ ሠርቶም ከበባት።


እንዲህም አለ፤ “አንቺ ለሰላምሽ የሚያስፈልገውን ነገር ምነው ዛሬ ዐውቀሽ ቢሆን ኖሮ! አሁን ግን ይህ ነገር ከዐይንሽ ተሰውሮብሻል፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements