Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 16:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ይህም ድኻ፥ ከሀብታሙ ማእድ የሚወድቀውን ፍርፋሪ ለመመገብ ይመኝ ነበር፤ ውሾችም እየመጡ ቊስሉን ይልሱ ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከሀብታሙ ሰው ማእድ የወደቀውን ፍርፋሪ እንኳ ሊመገብ ይመኝ ነበር፤ ውሾችም ሳይቀሩ መጥተው ቍስሉን ይልሱ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከሀብታሙም ማዕድ ከሚወድቀው ፍርፋሪ ለመጥገብ ይመኝ ነበር፤ ውሾች እንኳ መጥተው ቁስሎቹን ይልሱ ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ከባ​ለ​ጸ​ጋው ማዕድ የሚ​ወ​ድ​ቀ​ው​ንም ፍር​ፋሪ ሊመ​ገብ ይመኝ ነበር፤ ውሾ​ችም እየ​መጡ ቍስ​ሉን ይል​ሱት ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ከባለ ጠጋውም ማዕድ ከሚወድቀው ፍርፋሪ ሊጠግብ ይመኝ ነበር፤ ውሾች እንኳ መጥተው ቍስሎቹን ይልሱ ነበር።

See the chapter Copy




ሉቃስ 16:21
7 Cross References  

እርስዋም “ጌታ ሆይ! እርግጥ ነው፤ ነገር ግን ውሾችም ከጌቶቻቸው ማእድ የሚወድቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ” አለች።


ብዙ ሥራና ድካም ነበረብኝ፤ ብዙ ጊዜ እንቅልፍ አጥቻለሁ፤ በራብና በውሃ ጥም ተጨንቄአለሁ፤ ብዙ ጊዜም የምግብ እጦት ደርሶብኛል፤ ብርድና መራቆትም ደርሶብኛል።


አሁንም ቢሆን እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፤ እንጠማለን፤ እንራቈታለን፤ እንደበደባለን፤ መጠለያ በማጣት እንንከራተታለን።


ሁሉም በልተው ከጠገቡ በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፥ “አንድም ነገር እንዳይባክን የተረፈውንም ፍርፋሪ ሰብስቡ” አላቸው።


እርስዋም “እርግጥ ነው ጌታዬ፤ ግን ውሾችም እኮ በገበታ ሥር ሆነው ልጆች ሲበሉ የሚወድቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ፤” ስትል መለሰችለት።


መላ ሰውነቱ በቊስል የተወረሰ አልዓዛር የሚባል አንድ ድኻ ደግሞ በሀብታሙ ቤት ደጃፍ ተኝቶ ነበር፤


“ከዚህም በኋላ ድኻው ሰው ሞተ፤ መላእክትም ወደ አብርሃም አጠገብ ወሰዱት፤ እንዲሁም ሀብታሙ ሰው ሞተና ተቀበረ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements