Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 14:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የግብዣው ሰዓት በደረሰ ጊዜ፥ ‘እነሆ፥ ሁሉ ነገር ተዘጋጅቶአልና ወደ ግብዣው ኑ!’ ብሎ እንዲነግራቸው ጋባዡ አገልጋዩን ወደ ተጠሩት ሰዎች ላከው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የግብዣውም ሰዓት በደረሰ ጊዜ የተጋበዙትን እንግዶች፣ ‘እነሆ፤ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቷልና ኑ’ ብሎ እንዲጠራ ባሪያውን ላከባቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በእራትም ሰዓት የታደሙትን ‘አሁን ሁሉ ተዘጋጅቶአልና ኑ’ እንዲላቸው አገልጋዩን ላከ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ለምሳ የተ​ጠ​ሩ​በ​ትም ቀን በደ​ረሰ ጊዜ የታ​ደ​ሙ​ትን ይጠ​ራ​ቸው ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዩን ላከ፤ እር​ሱም ሄዶ የታ​ደ​ሙ​ትን፦ አሁን ምሳ​ውን ፈጽ​መን አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ና​ልና ኑ አላ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በእራትም ሰዓት የታደሙትን፦ አሁን ተዘጋጅቶአልና ኑ እንዲላቸው ባሪያውን ላከ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 14:17
17 Cross References  

ይህም ሁሉ የሆነው እኛን ከራሱ ጋር በክርስቶስ አማካይነት ባስታረቀንና የማስታረቅንም አገልግሎት በሰጠን በእግዚአብሔር ነው።


“እናንተ ከአብርሃም ዘር የተወለዳችሁ ወንድሞችና እናንተም እግዚአብሔርን የምትፈሩ አሕዛብ! ይህ የመዳን ቃል የተላከው ለእኛ ነው።


የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን ኢየሱስ ቆመና ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “ውሃ የጠማው ቢኖር ወደ እኔ መጥቶ ይጠጣ፤


ኢየሱስ ግን እንዲህ አለው፤ “አንድ ሰው ትልቅ የእራት ግብዣ አዘጋጅቶ፥ ብዙ ሰዎችን ጠራ፤


ነገር ግን እያንዳንዱ ተጋባዥ ከግብዣው ለመቅረት ምክንያት መስጠት ጀመረ፤ አንዱ ‘መሬት ስለ ገዛሁ ሄጄ ማየት አለብኝ፤ ስለዚህ መምጣት አልችልምና ይቅርታ አድርግልኝ’ አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements