ሉቃስ 13:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ኢየሱስ በሰንበት ቀን ስለ ፈወሰ የምኲራቡ አለቃ ተቈጣና ለሕዝቡ፦ “በሳምንት ውስጥ ሥራ የሚሠራባቸው ስድስት ቀኖች አሉ፤ በእነዚህ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ፤ በሰንበት ቀን ግን አይሆንም” ብሎ ተናገረ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 የምኵራቡ አለቃ ግን፣ ኢየሱስ በሰንበት ቀን ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ ሕዝቡን፣ “ሥራ ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ ስለዚህ በእነዚያ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት ቀን አይደለም” አላቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 የምኵራብ አለቃው ግን ኢየሱስ በሰንበት ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ ሕዝቡን “ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ እንግዲህ በእነርሱ መጥታችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት አይሆንም፤” አለ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 የምኵራቡ ሹምም ጌታ ኢየሱስ በሰንበት ፈውሶአልና፤ እየተቈጣ መልሶ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፥ “ሥራችሁን የምትሠሩባቸው ስድስት ቀኖች ያሉ አይደለምን? ያንጊዜ ኑና ተፈወሱ፤ በሰንበት ቀን ግን አይሆንም።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 የምኵራብ አለቃ ግን ኢየሱስን በሰንበት ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ መለሰና ሕዝቡን፦ ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ እንግዲህ በእነርሱ መጥታችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት አይደለም አለ። See the chapter |