Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 10:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ጌታ ኢየሱስ ግን እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “ማርታ፥ ማርታ፥ አንቺ በብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ትታወኪያለሽም፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ጌታ ግን እንዲህ ሲል መለሰላት፤ “ማርታ፣ ማርታ፤ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ትዋከቢአለሽም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላት፦ “ማርታ! ማርታ! በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪያለሽም፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትደ​ክ​ሚ​ያ​ለሽ፥ ትቸ​ገ​ሪ​ያ​ለ​ሽም፤ ታዘ​ጋ​ጂ​ያ​ለ​ሽም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥

See the chapter Copy




ሉቃስ 10:41
13 Cross References  

ስለዚህ ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፥ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ።


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።


ይሁን እንጂ የዚህ ዓለም ሐሳብ፥ የሀብት ፍቅርና ሌላውም ከንቱ ምኞት ወደ ልባቸው ገብቶ ቃሉን ስለሚያንቀው ያለ ፍሬ ይቀራል።


ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ “ስለዚህ ለሕወታችሁ ‘ምን እንበላለን? ለሰውነታችሁም ምን እንለብሳለን?’ በማለት ስለ ኑሮአችሁ አትጨነቁ እላችኋለሁ።


በእሾኽም ቊጥቋጦ መካከል የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ቃሉን ለጊዜው የሚሰሙትን ሰዎች ነው፤ ነገር ግን የዚህ ዓለም ሐሳብና ሀብት፥ የምድራዊ ኑሮ ምቾትም አንቆ ያለ ፍሬ ያስቀራቸዋል።


ብዙ በተናገርን መጠን ቁምነገሩ ያነሰ ነው፤ ስለዚህ የመናገር ጥቅሙ ምንድን ነው?


ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መንገዱን ቀጥሎ ወደ አንዲት መንደር ደረሰ፤ በዚያም ማርታ የምትባል አንዲት ሴት በቤትዋ ተቀበለችው፤


ማርታ ግን ምግብ በማዘጋጀት በብርቱ ትደክም ነበር፤ ስለዚህ ወደ ኢየሱስ ቀርባ፥ “ጌታ ሆይ! ይህች እኅቴ ሥራውን ሁሉ ለእኔ ትታ ብቻዬን ስደክም እያየህ ዝም ትላለህን? እባክህ እንድታግዘኝ ንገራት!” አለችው።


በቢታንያ የሚኖር አልዓዛር የሚባል አንድ ሰው ታሞ ነበር፤ ቢታንያ ማርያምና እኅትዋ ማርታ የሚኖሩባት መንደር ነበረች።


ኢየሱስ ማርታንና እኅትዋን ማርያምን ወንድማቸውን አልዓዛርንም ይወድ ነበር።


በዚያ ራት አዘጋጁለት፤ ማርታ ታገለግል ነበር፤ አልዓዛርም ከኢየሱስ ጋር በማእድ ቀርበው ከነበሩት አንዱ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements