Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 10:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መንገዱን ቀጥሎ ወደ አንዲት መንደር ደረሰ፤ በዚያም ማርታ የምትባል አንዲት ሴት በቤትዋ ተቀበለችው፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ መንገድ ሲሄዱ፣ ኢየሱስ ወደ አንድ መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤቷ ተቀበለችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 በጉዞአቸውም ላይ ሳሉ እርሱ ወደ አንዲት መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤትዋ ተቀበለችው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ከዚ​ህም በኋላ ሄደው ወደ አን​ዲት መን​ደር ገቡ፤ ማርታ የም​ት​ባል አን​ዲት ሴትም በቤቷ ተቀ​በ​ለ​ችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ሲሄዱም እርሱ ወደ አንዲት መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤትዋ ተቀበለችው።

See the chapter Copy




ሉቃስ 10:38
10 Cross References  

እርስዋና በቤትዋ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ፥ “በጌታ የማምን መሆኔን ካረጋገጣችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ተቀመጡ” ስትል አጥብቃ ለመነችን።


ይህን ትምህርት ሳይዝ ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት፤ ሰላምታም እንኳ አትስጡት።


የሕግ መምህሩም “ያ የራራለትና የረዳው ነው፤” ሲል መለሰ፤ ኢየሱስም “እንግዲያውስ ሂድ፤ አንተም እንዲሁ አድርግ!” አለው።


ማርታ ግን ምግብ በማዘጋጀት በብርቱ ትደክም ነበር፤ ስለዚህ ወደ ኢየሱስ ቀርባ፥ “ጌታ ሆይ! ይህች እኅቴ ሥራውን ሁሉ ለእኔ ትታ ብቻዬን ስደክም እያየህ ዝም ትላለህን? እባክህ እንድታግዘኝ ንገራት!” አለችው።


ጌታ ኢየሱስ ግን እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “ማርታ፥ ማርታ፥ አንቺ በብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ትታወኪያለሽም፤


ኢያሶንም ተቀብሎአቸዋል፤ ‘ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አለ’ እያሉም የሮምን ንጉሠ ነገሥት ትእዛዝ ይቃወማሉ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements