Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 8:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እግዚአብሔርም ለኢያሱ በነገረው መሠረት እስራኤላውያን በዚያች ያገኙትን የከብትና የሌላ ንብረት ምርኮ ሁሉ ለራሳቸው አደረጉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ኢያሱን ባዘዘው መሠረት፣ በከተማዪቱ ያገኙትን እንስሳትና ምርኮ ብቻ ለራሳቸው አደረጉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ነገር ግን ጌታ ኢያሱን ባዘዘው ቃል መሠረት የዚያችን ከተማ ከብትና ምርኮ ብቻ እስራኤል ለራሳቸው ዘረፉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን እን​ዳ​ዘ​ዘው የዚ​ያ​ችን ከተማ ከብ​ትና ምርኮ ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለራ​ሳ​ቸው ዘረፉ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ነገር ግን እግዚአብሔር ኢያሱን እንዳዘዘው ቃል የዚያችን ከተማ ከብትና ምርኮ እስራኤል ለራሳቸው ዘረፉ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 8:27
8 Cross References  

ከዚህ በፊት በኢያሪኮና በንጉሥዋ ላይ የደረሰውን ጥፋት በዐይና በንጉሥዋም ላይ ደግሞ ትፈጽምባቸዋለህ፤ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ከእርስዋ የሚገኘውን የንብረትና የከብት ምርኮ ለራሳችሁ ታደርጋላችሁ፤ ከኋላ በኩል በከተማይቱ ላይ በድንገት አደጋ ለመጣል ተዘጋጅ።”


በገዛ ገንዘቤ የፈለግኹትን ማድረግ መብት የለኝምን? ወይስ እኔ ለጋሥ ስለ ሆንኩ አንተ ትመቀኛለህ?’ ”


በዱር ያሉ አራዊትና በሺህ የሚቈጠሩ ተራራዎች ላይ የሚሰማሩት የእንስሶች መንጋዎች የእኔ ናቸው።


እነርሱም ከነወታደሮቻቸው ስለ መጡ፥ የሠራዊቱ ብዛት እንደ ባሕር አሸዋ ሆነ፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ነበራቸው።


“አንተና አልዓዛር ከቀሩት የማኅበሩ መሪዎች ጋር በመሆን እስረኞችንና እንስሶችን ጭምር በምርኮ የተገኘውን ማንኛውንም ነገር ቊጠሩ።


እንደ ወርቅ፥ ብር፥ ነሐስ፥ ብረት፥ ቆርቆሮ ወይም እርሳስ የመሳሰሉ እሳት የማይጐዳቸው ነገሮች በእሳት ውስጥ አልፈው መጥራት ይኖርባቸዋል፤ እሳት መቋቋም የማይችለውን ነገር ሁሉ ለመንጻት ሥርዓት በተመደበው ውሃ ታጠሩታላችሁ።


ኢያሱ የዐይን ከተማ በማቃጠል ለዘለዓለም ፍርስራሽ አድርጎ ተዋት፤ እስከ አሁንም ድረስ በዚህ ዐይነት ትገኛለች።


ከብቱን ሁሉ ማርከን ወሰድን፤ ከተሞችንም በዘበዝን።


Follow us:

Advertisements


Advertisements