Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 8:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እነርሱም ዋናውን ሠራዊት ከከተማ በስተሰሜን በኩል፥ የኋላውን ደጀን በስተምዕራብ በኩል አሰለፉ፤ ኢያሱ ግን ሌሊቱን በሸለቆው አሳለፈ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከከተማዪቱ በስተሰሜን የነበሩትንም፣ ከከተማዪቱ በስተምዕራብ የሸመቁትንም ወታደሮች ሁሉ ስፍራ ስፍራቸውን እንዲይዙ አደረጋቸው፤ በዚያችም ሌሊት ኢያሱ ወደ ሸለቆው ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በከተማይቱ በሰሜን በኩል የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ በከተማይቱም በምዕራብ በኩል የኋላ ደጀን የሆነውን ሕዝብ አኖሩ፤ ኢያሱም በዚያች ሌሊት በሸለቆው ውስጥ አደረ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሕዝ​ቡም ሁሉ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን በከ​ተ​ማው መስዕ በኩል አኖሩ፤ ዳር​ቻ​ውም እስከ ከተ​ማው ባሕር ድረስ ነው፤ ኢያ​ሱም በዚ​ያች ሌሊት ወደ ሸለ​ቆው መካ​ከል ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በከተማይቱ በሰሜን በኩል የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ በከተማይቱም በምዕራብ በኩል የተደበቁትን ሕዝብ አኖሩ፥ ኢያሱም በዚያች ሌሊት ወደ ሸለቆው መካከል ሄደ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 8:13
3 Cross References  

ኢያሱ አምስት ሺህ ሰዎችን ያኽል መርጦ ከከተማይቱ በስተምዕራብ በኩል በዐይና በቤትኤል መካከል እንዲሸምቁ አድርጎ ነበር።


ከተማይቱን ከያዛችሁ በኋላ፥ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በእሳት አቃጥሉአት። እነሆ፥ አዝዤአችኋለሁ።”


የዐይ ንጉሥ ይህን በአየ ጊዜ እርሱና የከተማው ሕዝብ እስራኤልን በጦርነት ለመግጠም ወደ ዓራባ ፊት ለፊት ወጡ። ከከተማው በስተጀርባ በኩል የደጀን ጦር መኖሩን አላወቁም ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements