Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 24:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ኢያሱም “እንግዲህ እግዚአብሔርን ለማምለክ ስለ መምረጣችሁ ራሳችሁ በራሳችሁ ላይ ምስክሮች ናችሁ” ሲል ነገራቸው። እነርሱም “አዎ፤ ምስክሮች ነን፤” አሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከዚያም ኢያሱ፣ “እንግዲህ እግዚአብሔርን ለማምለክ መርጣችኋልና በራሳችሁ ላይ ምስክሮች ናችሁ” አላቸው። እነርሱም፣ “አዎን ምስክሮች ነን” ሲሉ መለሱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “እንድታገለግሉት እናንተ ጌታን እንደ መረጣችሁ በራሳችሁ ላይ ምስክሮች ናችሁ፤” እነርሱም፦ “ምስክሮች ነን” አሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን፥ “እን​ድ​ታ​መ​ል​ኩት እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ መረ​ጣ​ችሁ በራ​ሳ​ችሁ ላይ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “ምስ​ክ​ሮች ነን” አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ኢያሱም ሕዝቡን፦ እንድታመልኩት እናንተ እግዚአብሔርን እንደ መረጣችሁ በራሳችሁ ላይ ምስክሮች ናችሁ አላቸው፥ እነርሱም፦ ምስክሮች ነን አሉ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 24:22
7 Cross References  

ትእዛዞችህን ስለ መረጥኩ፥ እኔን ለመርዳት ዘወትር ዝግጁ ሁን።


አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ አኖራለሁ።


ነገር ግን ተፈላጊው አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያም የሚሻለውን ነገር መርጣለች፤ እርሱንም ከእርስዋ የሚወስድባት ማንም የለም።”


የሚፈርድብህ የገዛ አንደበትህ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም፤ አነጋገርህም ያጋልጥሃል።


እግዚአብሔር አምላክህ መሆኑንና በሕጉም የምትመራ መሆንህን ዛሬ አንተ አረጋግጠሃል፤ ሥርዓቱን፥ ትእዛዞቹንና ሕጎቹን ለመጠበቅና ታዛዥ ለመሆን ቃል ገብተሃል፤


ጌታውም ‘አንተ መጥፎ አገልጋይ! በአነጋገርህ እፈርድብሃለሁ፤ እኔ ያላስቀመጥኩትን የምወስድና ያልዘራሁትን የምሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆኔን ዐውቀሃል፤


ሕዝቡም ለኢያሱ “ይህ ከቶ አይደረግም! እኛ እግዚአብሔርን እናመልካለን” አሉት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements