ኢያሱ 22:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 እስራኤላውያንም በመልሱ ረክተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከዚያም በኋላ የሮቤልና የጋድ ሕዝብ የሚኖሩባትን ምድር ለመደምሰስ ጦርነት ስለ ማንሣት ጉዳይ መናገር አልፈለጉም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም33 እስራኤላውያንም ይህን ሲሰሙ ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከዚያም የሮቤልና የጋድ ወገኖች የሚኖሩበትን አገር በጦርነት ለማጥፋት የመሄድን ነገር አላነሡም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 ነገሩም የእስራኤልን ልጆች ደስ አሰኘ፤ የእስራኤልም ልጆች ጌታን አመሰገኑ፥ ከዚያም ወዲያ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የተቀመጡባትን ምድር ለማጥፋት ወጥተን እንወጋታለን ብለው አልተናገሩም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 ነገሩም የእስራኤልን ልጆች ደስ አሰኘ፤ ለእስራኤልም ልጆች በነገሩአቸው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከዚያም ወዲያ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ የተቀመጡባትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ለመውጋት አንወጣም ተባባሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 ነገሩም የእስራኤልን ልጆች ደስ አሰኘ፥ የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን አመሰገኑ፥ ከዚያም ወዲያ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የተቀመጡባትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ወጥተው እንዲወጉአቸው አልተናገሩም። See the chapter |