ኢያሱ 20:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ሊበቀለው የሚፈልገው ሰው ቢያሳድደው፥ ሰውን የገደለው በድንገተኛ አጋጣሚ እንጂ በቂም በቀል ተነሣሥቶ ስላይደለ የከተማይቱ ሰዎች እርሱን አሳልፈው መስጠት አይገባቸውም፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ደም ተበቃዩ ተከታትሎት ቢመጣ፣ ሆነ ብሎና በክፋት ተነሣሥቶ ወንድሙን የገደለው ባለመሆኑ፣ ሰዎቹ ነፍሰ ገዳዩን አሳልፈው አይስጡት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ደም ተበቃዩ ቢያሳድደው፥ አስቀድሞ ሳይጠላው ባልንጀራውን ሳያውቅ ስለ ገደለው ነፍሰ ገዳዩን በእጁ አሳልፈው አይስጡት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ባለ ደሙ ቢያሳድደው፥ አስቀድሞ ሳይጠላው ባልንጀራውን በስሕተት ስለ ገደለው ነፍሰ ገዳዩን በእጁ አሳልፈው አይስጡት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ደም ተበቃዩ ቢያሳድደው፥ አስቀድሞ ሳይጠላው ባልንጀራውን በስሕተት ስለ ገደለው ነፍሰ ገዳዩን በእጁ አሳልፈው አይስጡት። See the chapter |