Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 19:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የይሁዳ ነገድ ድርሻ በጣም ብዙ ስለ ነበር ለስምዖን ነገድ በይሁዳ ርስት ውስጥ ድርሻ ተሰጠው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የይሁዳ ነገድ የያዘው ርስት እጅግ ሰፊ ስለ ነበር፣ ከይሁዳ ነገድ ድርሻ ተከፍሎ ለስምዖን ነገድ በርስትነት ተሰጠ። ከዚህ የተነሣም የስምዖን ነገድ በይሁዳ ነገድ ድርሻ ርስት ሊካፈል ቻለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የይሁዳ ልጆች ግዛት በሆነው ክፍል ውስጥ የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ፥ የይሁዳም ልጆች ድርሻ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ከይ​ሁዳ ልጆች ክፍል የስ​ም​ዖን ልጆች ርስት ሆነ፤ የይ​ሁ​ዳም ልጆች ዕድል ፋንታ ስለ በዛ​ባ​ቸው የስ​ም​ዖን ልጆች በር​ስ​ታ​ቸው መካ​ከል ወረሱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ፥ የይሁዳም ልጆች እድል ፈንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 19:9
7 Cross References  

በሰፈሩትም ጊዜ ብዙ የሰበሰበው አልተረፈውም፤ ጥቂትም የሰበሰበ አላነሰበትም፤ እያንዳንዱ የሰበሰበው ልክ የሚበቃውን ያኽል ነበር።


እጅግ አስፈሪ የሆነ ቊጣቸው፥ እጅግ ጨካኝ የሆነ መዓታቸው፥ የተረገመ ይሁን። በእስራኤል ምድር ሁሉ እበታትናቸዋለሁ፤ በሕዝቡም መካከል እከፋፍላቸዋለሁ።


በደቡብ በኩል እስከምትገኘው እስከ ባዕላትበኤር (ራማ) ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ያሉትን ትንንሽ ከተሞችን ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የስምዖን ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይዞ ነበር፤


ሦስተኛው ዕጣ ለዛብሎን ነገድ በየወገናቸው ወጣ፤ እነርሱም የተቀበሉት ርስት እስከ ሣሪድ ይደርሳል፤


ይሁዳ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከሮቤል ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል።


ብዛት ላለው ነገድ ሰፊ መሬት፥ አነስተኛ ቊጥር ለሆነ ነገድ ጠበብ ያለ መሬት ስጥ፤ የርስቱም ክፍፍል በቈጠራ በተገኘው የሕዝብ ብዛት መሠረት ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements