Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 15:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ዖትኒኤልም በሠርጋቸው ቀን ዓክሳን ከአባትዋ የእርሻ መሬት እንድትለምን መከራት፤ እርስዋም ከበቅሎዋ ላይ ወረደች፤ (መሳ 1፥14 ተመልከት) ካሌብም “ምን ትፈልጊአለሽ” ሲል ጠየቃት፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ዓክሳ ወደ ጎቶንያል በመጣች ጊዜም፣ ከአባቷ ላይ የዕርሻ መሬት እንዲለምን አጥብቃ ነገረችው። ከአህያዋ ላይ እንደ ወረደች ካሌብ፣ “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እርሷም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ እንዲለምን መከረችው፤ እርሷም ከአህያዋ ወረደች፤ ካሌብም፦ “ምን ፈለግሽ?” አላት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እር​ስ​ዋም ወደ እርሱ በመ​ጣች ጊዜ “አባ​ቴን እርሻ ልለ​ም​ነው” ብላ አማ​ከ​ረ​ችው፤ እር​ስ​ዋም በአ​ህ​ያዋ ላይ ሆና ጮኸች፤ ካሌ​ብም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እርስዋም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ እንዲለምን መከረችው፥ እርስዋም ከአህያዋ ወረደች፥

See the chapter Copy




ኢያሱ 15:18
4 Cross References  

አቢጌልም ዳዊትን ባየችው ጊዜ በፍጥነት ከአህያዋ ወርዳ በዳዊት ጫማ አጠገብ መሬት ላይ ለጥ ብላ እጅ ነሣች፤


ርብቃ ይስሐቅን ባየች ጊዜ ከግመሏ ወረደችና፥


እርስዋም “የሰጠኸኝ ምድር ደረቅ ስለ ሆነ ጥቂት የውሃ ጒድጓዶች እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ” አለችው። ካሌብም ከላይና ከታች በኩል ያሉትን ሁለቱን የውሃ ምንጮች ሰጣት።


በጋብቻቸውም ቀን ዖትኒኤል ዓክሳን “አባትሽ የእርሻ መሬት እንዲሰጥሽ ጠይቂ” አላት፤ እርስዋም ካሌብን ስታይ ከበቅሎዋ ላይ ወረደች፤ ካሌብም “ምን እንድሰጥሽ ትፈልጊአለሽ” ብሎ ጠየቃት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements