Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 14:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ነገድ የቤተሰብ አለቆች በከነዓን ምድር ለእስራኤላውያን አከፋፍለዋቸው የተቀበሉት ርስት ይህ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ካህኑ አልዓዛር፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል የየነገዱ ጐሣ አባቶች የደለደሉላቸው፣ እስራኤላውያንም በከነዓን ምድር የወረሱት ርስት ይህ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የእስራኤልም ልጆች በከነዓን ምድር የወረሱት፥ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ የእስራኤልም ልጆች ነገድ የአባቶቻቸው አለቆች ያከፋፈሉአቸው ርስት ይህ ነው፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ነ​ዓን ምድር የወ​ረ​ሱት ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርና የነዌ ልጅ ኢያሱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ነገድ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አለ​ቆች ያወ​ረ​ሱ​አ​ቸው ርስት ይህ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የእስራኤልም ልጆች በከነዓን ምድር የወረሱት፥ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ የእስራኤልም ልጆች ነገድ የአባቶቻቸው አለቆች ያካፈሉአቸው ርስት ይህ ነው፥

See the chapter Copy




ኢያሱ 14:1
10 Cross References  

ከዚያም በኋላ በከነዓን አገር ሰባት መንግሥታትን አጥፍቶ የእነርሱን ምድር አወረሳቸው፤


ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ለዘጠኝ ተኩል ነገዶች እንዲሰጥ እግዚአብሔር ያዘዘው በዕጣ የምትካፈሉት ርስት ይህ ነው።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤


እግዚአብሔር አምላካችሁ በሰጣችሁ ምድር ለመኖር ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፤ በደኅና እንድትኖሩ በዙሪያ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉ ዕረፍት ይሰጣችኋል፤


ከሊባኖስ እስከ ሚስረፎትማይም ድረስ በተራራማው አገር የሚኖሩ ነዋሪዎች፥ ማለት ሲዶናውያንን ሁሉ፥ እኔ ራሴ ከእስራኤላውያን ፊት አባርራቸዋለሁ፤ አንተ ግን እኔ እንዳዘዝኩህ ምድሪቱን ለእስራኤላውያን ርስት አድርገህ አከፋፍል።


ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ የነገድ አለቆች በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ለእስራኤል ሕዝብ በዕጣ ያከፋፈሉት ርስት ይህ ነው። በዚህም ዐይነት ምድሪቱን አከፋፍለው ጨረሱ።


የሌዊ ነገድ ቤተሰቦች መሪዎች ወደ ካህኑ አልዓዛር፥ ወደ ነዌ ልጅ ኢያሱና ወደ እስራኤል ሕዝብ የነገድ መሪዎች ሄዱ፤


ቡቂ የአቢሹዓ ልጅ፥ አቢሹዓ የፊንሐስ ልጅ፥ ፊንሐስ የአልዓዛር ልጅ፥ አልዓዛር የሊቀ ካህናቱ የአሮን ልጅ ነው።


ምድሪቱ ለእያንዳንዱ ነገድ በርስትነት በምትከፋፈልበት ጊዜ አንድ ዕጣ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል፤ እርሱም ርዝመቱ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ፥ ወርዱም ኻያ ሺህ ክንድ ይሆናል፤ ጠቅላላውም ክልል የተቀደሰ ይሆናል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements