Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 13:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ይህ ሁሉ ሲሆን፥ ሙሴ ለሌዊ ነገድ የሚሰጥ የርስት ድርሻ አልመደበም፤ የእነርሱ ርስት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ ድርሻቸውን የሚያገኙት ለእግዚአብሔር ከሚቀርበው መሥዋዕት መሆኑን ነግሮአቸዋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ለሌዊ ነገድ ግን ሙሴ ርስት አልሰጠም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው እርሱ ራሱ ርስታቸው ነውና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ለሌዊ ነገድ ግን ሙሴ ርስት አልሰጠም፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንደ ነገራቸው እንዲሁ ርስታቸው እርሱ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ለሌዊ ነገድ ግን ሙሴ ርስት አልሰጠም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳላቸው ርስታቸው እርሱ ነው።

See the chapter Copy




ኢያሱ 13:33
7 Cross References  

ይሁን እንጂ የሌዋውያን ድርሻ ካህናት ሆነው እግዚአብሔርን ማገልገል ስለ ሆነ እነርሱ ከሌሎቻችሁ ጋር የርስት ድርሻ አይኖራቸውም፤ የሮቤልና የጋድ እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ በኩል የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የሰጣቸውን ርስት አስቀድመው ወርሰዋል።”


ሙሴ ለሌዊ ነገድ የርስት ድርሻ አልሰጠም፤ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር በመሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ ከሚቀርበው መባ የሚያገኙት ድርሻ እንደ ርስት ሆኖ ተመድቦላቸዋል።


የሌዊ ነገድ ከሌሎቹ ወንድሞቹ ጋር ርስት እንዲኖረው ያልተደረገበትም ምክንያት ይኸው ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ አስቀድሞ እንደ ተናገረ ካህናት ሆነው የማገልገልን መብት በማግኘታቸው ራሱ እግዚአብሔር ለሌዋውያን ርስታቸው ነው።)


እግዚአብሔር አሮንን እንዲህ አለው፦ “ለትውልድ የሚተላለፍ ምንም ዐይነት ርስት አትቀበልም፤ ከእስራኤልም ምድር የትኛውም ክፍል ለአንተ አይሆንም፤ እኔ እግዚአብሔር ራሴ ለአንተ ርስትህ ነኝ።”


በሞአብ ሜዳ በነበረበት ጊዜ ሙሴ በኢያሪኮና በዮርዳኖስ ምሥራቅ ወንዝ ያለውን ምድር ያከፋፈለው በዚህ ዐይነት ነበር።


“ይህ የካህናቱ ርስት ነው፤ ይህም ማለት እኔ ርስታቸው ነኝ፤ እኔ ይዞታቸው ስለ ሆንኩ በእስራኤል ምንም ይዞታ አይሰጣቸውም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements