ኢያሱ 12:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ግዛቱም የሔርሞንን ተራራ፥ ሳለካን፥ እስከ ገሹርና ማዕካ ድንበሮች የሚደርሰውን የባሳንን ምድር ሁሉ ጠቅልሎ፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሲሖን ይዞታ እስከሆነው ግዛት የገለዓድን እኩሌታ የሚጨምር ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 የአርሞንዔምን ተራራ፣ ሰልካንን፣ ባሳንን ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ድንበሮች እንዲሁም ከገለዓድ እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ወሰን ድረስ ገዝቷል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ይገዛ የነበረው የአርሞንዔምን ተራራ፥ ሰልካን፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የአርሞንኤምን ተራራ፥ ካሴኪን፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌርጌሲና እስከ መከጢ ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ የገዛው የባሳን ንጉሥ ዐግ፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ሰልካን፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ የገዛው የባሳን ንጉሥ ዐግ። See the chapter |