ኢያሱ 11:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እነርሱም ከነወታደሮቻቸው ስለ መጡ፥ የሠራዊቱ ብዛት እንደ ባሕር አሸዋ ሆነ፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ነበራቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 እነዚህም ሰራዊታቸውን ሁሉ እጅግ ብዙ ከሆኑ ፈረሶችና ሠረገሎች ጋራ ይዘው ወጡ፤ የሰራዊቱም ብዛት በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 እነዚህም ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ፥ በቍጥር ም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ከሚሆን ብዙ ሕዝብ፥ እጅግም ከሚበዙ ፈረሶችና ሰረገሎች ጋር በመሆን ወጡ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 እነርሱ፥ ከእነርሱም ጋር ሠራዊቶቻቸው ሁሉ ብዛታቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆነው ወጡ፤ ፈረሶችና ሰረገሎችም እጅግ ብዙዎች ነበሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 እነዚህም ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ከእጅግም ብዙ ፈረሰኞና ሠረገሎች ጋር ወጡ፥ በባሕር ዳርም እንዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበረ። See the chapter |