ኢያሱ 11:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ስምምነት አድርጋ በሰላም የኖረች አገር ከሒዋውያን ወገን የገባዖን ኑዋሪዎች በቀር ሌላ አልነበረም፤ ሌሎቹ በሙሉ በጦርነት ድል ሆነው የተያዙ ናቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዊያውያን በቀር፣ ከእስራኤላውያን ጋራ የሰላም ውል ያደረገ አንድም ከተማ አልነበረም፤ ሁሉንም የያዙት በጦርነት ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዊያውያን በቀር ከእስራኤል ልጆች ጋር ዕርቅ ያደረገች አንዲት ከተማ አልነበረችም፤ ሁሉንም በጦርነት ድል አድርገው ያዙ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዎናውያን በቀር፤ እስራኤል ያልያዙት ከተማ አልነበረም፥ ሁሉን በጦርነት ያዙ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዊያውያን በቀር ከእስራኤል ልጆች ጋር ዕርቅ ያደረገች አንዲት ከተማ አልነበረችም፥ ሁሉን በሰልፍ ያዙ። See the chapter |