ኢያሱ 1:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ይህን የሕግ መጽሐፍ ምን ጊዜም ከማንበብ አትቈጠብ፤ በእርሱ የተጻፈውን ሁሉ መፈጸም ትችል ዘንድ እርሱን ሌሊትና ቀን አሰላስለው፤ ይህንን ብታደርግ፥ ሁሉ ነገር በተቃና ሁኔታ ይሳካልሃል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤ በውስጡ የተጻፈውን ሁሉ በጥንቃቄ እንድትፈጽመውም ቀንም ሆነ ሌት ከሐሳብህ አትለየው፤ ይህን ካደረግህ ያሰብኸው ይቃናል፤ ይሳካልም፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአንደበትህ አይለይ፥ ነገር ግን በእርሱ ውስጥ የተጻፈውን ሁሉ እንድትጠብቅና እንድታደርገው በቀንም በሌሊትም አሰላስለው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቃናልሃል ይከናወንልሃልም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አንብበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል፤ አስተዋይም ትሆናለህ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፥ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። See the chapter |