Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 1:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፤ “የነገርከንን ሁሉ እንፈጽማለን፤ ወደምትልከንም ስፍራ ሁሉ እንሄዳለን፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ያዘዝኸንን ሁሉ እናደርጋለን፤ ወደምትልከንም ሁሉ እንሄዳለን።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፦ “ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን ወደምትልከንም ስፍራ ሁሉ እንሄዳለን።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እነ​ር​ሱም ለኢ​ያሱ እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ለት፥ “ያዘ​ዝ​ኸ​ንን ነገር ሁሉ እና​ደ​ር​ጋ​ለን ወደ​ም​ት​ል​ከ​ንም ስፍራ እን​ሄ​ዳ​ለን።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፦ ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን ወደምትልከንም ስፍራ እንሄዳለን።

See the chapter Copy




ኢያሱ 1:16
10 Cross References  

ሰዎች ሁሉ ለገዢዎችና ለባለሥልጣኖች በትሕትና እንዲታዘዙ፥ መልካም ሥራን ሁሉ ለመሥራት ዝግጁዎች እንዲሆኑ፥


ስለዚህ ወደ እርሱ ቀርበህ እግዚአብሔር አምላካችን የሚለውን ሁሉ አዳምጥ፤ ተመልሰህም እርሱ ያለውን ሁሉ ንገረን፤ እኛም ሰምተን እንታዘዛለን።’


የጋድና የሮቤል ወገኖች እንዲህ አሉ፤ “እኛ አገልጋዮችህ፥ አንተ ጌታችን እንዳዘዝከው እናደርጋለን።


እግዚአብሔር አምላካችሁ ለእናንተ እንደ ሰጠው ለወንድሞቻችሁም ዕረፍትን እስኪሰጥና እነርሱም እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ርስት እስኪያገኙ አብራችሁ ዝመቱ። ከዚያ በኋላ ተመልሳችሁ መጥታችሁ፥ በምሥራቅ በኩል ከዮርዳኖስ ማዶ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሰጣችሁ በገዛ ምድራችሁ ትቀመጣላችሁ።”


ለሙሴ ሁልጊዜ ስንታዘዝለት እንደ ነበረ ሁሉ፥ ለአንተም እንታዘዛለን፤ እግዚአብሔር አምላክህ ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ፥ ከአንተም ጋር ይሁን!


የጋድና የሮቤል ሰዎችም እንዲህ ሲሉ መልስ ሰጡ፤ “እግዚአብሔር ያዘዘንን ሁሉ እናደርጋለን፤


ሙሴ የእርሱ ተተኪ እንዲሆን እጆቹን በመጫን ሹሞት ስለ ነበር የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ የተሞላ ሆነ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ለኢያሱ ታዘዘለት፤ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጣቸውንም ትእዛዝ ጠበቁ።


ይህንንም ሁሉ ለማስፈጸም ኀላፊነቱ የአንተ ስለ ሆነ ተነሥ፤ እኛም እንደግፍሃለን፤ አይዞህ በርታ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements