Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮናስ 4:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ነገር ግን በማግስቱ ጠዋት እግዚአብሔር አንድ ትል አዘጋጀ፤ ትልዋም ቅሊቱን በላች፤ እርሷም ደረቀች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ነገር ግን በሚቀጥለው ቀን በማለዳ እግዚአብሔር ትል አመጣ፤ ትሉም ቅሉን በላ፤ ቅሉም ደረቀ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በማግስቱ ግን ወገግ ባለ ጊዜ እግዚአብሔር ትልን አዘጋጀ፥ እርሷም የጉሎውን ተክል መታች፤ ደረቀም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በነ​ጋው ግን ወገግ ባለ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትልን አዘዘ፤ እር​ስ​ዋም ቅሊ​ቱን መታ​ቻት፤ ደረ​ቀ​ችም።

See the chapter Copy




ዮናስ 4:7
7 Cross References  

የወይን ተክሎችና የበለስ ዛፎች ጠውልገዋል፤ ሮማኑ፥ ተምሩና እንኰዩ፥ ሌሎችም የፍራፍሬ ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፤ በዚህም ምክንያት በእርግጥ ደስታ ከሰው ልጆች ርቆአል።


ይህም የሆነው ከፍ ከፍ ካደረግኸኝ በኋላ፥ ከኀይለኛ ቊጣህ የተነሣ ስለ ጣልከኝ ነው።


“ከእናቴ ማሕፀን ራቁቴን ተወለድኩ፤ ስሞትም ራቁቴን እሄዳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ወሰደ፤ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን!” አለ።


ጥላ በማግኘት ከፀሐይ ግለት እንዲድን እግዚአብሔር አምላክ አንድ የቅል ተክል አብቅሎ ቅጠሎችዋ ከዮናስ ራስ በላይ እንዲሆኑ አደረገ፤ ዮናስም ከቅሉ ሐረግ ጥላ በማግኘቱ እጅግ ተደሰተ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements