Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 5:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በኢየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ፥ በዕብራይስጥ ቋንቋ ቤተ ሳይዳ የሚባል አንድ የምንጭ ኲሬ ነበረ፤ በዙሪያውም አምስት ከላይ ክዳን ያላቸው መተላለፊያዎች ነበሩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በኢየሩሳሌም፣ በበጎች በር አጠገብ፣ ዐምስት ባለመጠለያ መመላለሻዎች የነበሯት፣ በአራማይክ ቋንቋ ቤተ ሳይዳ የተባለች አንዲት መጠመቂያ አለች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በበ​ጎች በር አጠ​ገብ መጠ​መ​ቂያ ነበ​ረች፤ ስም​ዋ​ንም በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉ​አ​ታል፤ አም​ስት እር​ከ​ኖ​ችም ነበ​ሩ​አት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 5:2
14 Cross References  

ከዚያም አልፈን የኤፍሬም ቅጽር በር፥ የይሻና ቅጽር በር፥ የዓሣ ቅጽር በር ተብለው ወደተሰየሙትና የሐናንኤል ግንብ የመቶዎቹ ግንብና የበጎች ቅጽር በር ተብለው ወደሚጠሩት ስፍራዎች መጣን፤ ሰልፋችንንም ያበቃነው ለቤተ መቅደሱ ቅርብ ወደ ሆነው የዘበኞች ቅጽር በር ወደሚባለው ቦታ ስንደርስ ነበር።


የከተማይቱ ቅጽር እንደገና የተሠራው በዚህ ዐይነት ነበር፦ ሊቀ ካህናቱ ኤልያሺብና የእርሱ ሥራ ባልደረቦች የሆኑት ካህናት “የበጎች በር” ተብሎ የሚጠራውን ቅጽር በር እንደገና ሠርተው ለእግዚአብሔር የተለየ አደረጉት፤ በሮችንም አበጁለት፤ ቅጽሩንም “መቶ” ተብሎ እስከሚጠራው የመጠበቂያ ግንብና “ሐናንኤል” ተብሎ እስከሚጠራው ሌላ የመጠበቂያ ግንብ ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ አደረጉት።


ወርቅ አንጥረኞችና ነጋዴዎችም ከቅጽሩ ማእዘን ጀምሮ እስከ በጎች ቅጽር በር ያለውን የመጨረሻውን ክፍል ሠሩ።


ከጥንቱ ኲሬ የሚወርደውን ውሃ ለመመለስ በከተማይቱ ውስጥ ግድብ ሠራችሁ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በመጀመሪያ ዐቅዶ ያደረገው እግዚአብሔር መሆኑ ትዝ አላላችሁም።


እንዲናገር በፈቀደለት ጊዜ ጳውሎስ በደረጃ ላይ ቆሞ ሕዝቡ ዝም እንዲል በእጁ ጠቀሰ፤ ሕዝቡ ጸጥ ባለ ጊዜ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ፤


ኢየሱስም “ማርያም!” አላት። እርስዋም ወደ እርሱ ዞር ብላ በዕብራይስጥ ቋንቋ “ረቡኒ!” አለችው፤ ትርጓሜውም “መምህር ሆይ!” ማለት ነው።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ መስቀሉን ተሸክሞ፥ “የራስ ቅል” ወደሚባለው ስፍራ ወጣ፤ ይህ ስፍራ በዕብራይስጥ ቋንቋ “ጎልጎታ” ይባላል፤


ጲላጦስ ይህን በሰማ ጊዜ ኢየሱስን ወደ ውጪ አውጥቶ “ጠፍጣፋ ድንጋይ” በተባለው ስፍራ በፍርድ ወንበር ተቀመጠ፤ ይህ ስፍራ በዕብራይስጥ ቋንቋ “ገበታ” ይባላል።


የዳዊት ከተማ ብዙ ፍርስራሾች መብዛታቸውን ተመልክታችኋል፤ ከታችኛውም ኩሬ ውሃ አጠራቀማችሁ።


ኢየሱስ የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ስለ ነበር፥ ከአይሁድ ብዙዎቹ ጽሑፉን አነበቡት፤ ጽሑፉም የተጻፈው በዕብራይስጥ፥ በላቲንና በግሪክ ቋንቋ ነበር።


[በጣም ብዙ በሽተኞች፥ ዕውሮች አንካሶችና ሽባዎች በመተላለፊያዎቹ ተኝተው ነበር። እነዚህ የውሃውን መንቀሳቀስ ይጠባበቁ ነበር፤


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔ አንድ ሥራ ሠራሁ፤ እናንተም ሁላችሁ በዚህ ሥራ ትደነቃላችሁ።


ንጉሥም ነበራቸው፤ እርሱ የጥልቁ ጒድጓድ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ አባዶን፥ በግሪክ አጶልዮን ይባላል፤


መናፍስቱም ነገሥታቱን በዕብራይስጥ አርማጌዶን በሚባል ስፍራ ሰበሰቡአቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements