Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 4:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ስለ እርሱ የተባለውን ፈሪሳውያን እንደ ሰሙ ባወቀ ጊዜ ኢየሱስ የይሁዳን ምድር ትቶ ወደ ገሊላ ተመልሶ ሄደ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ጌታም ይህን እንዳወቀ ይሁዳን ለቅቆ ወደ ገሊላ ተመልሶ ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የይሁዳን ምድር ትቶ ወደ ገሊላ እንደገና ሄደ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የይ​ሁ​ዳ​ንም ምድር ትቶ ዳግ​መኛ ወደ ገሊላ ሄደ።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 4:3
11 Cross References  

በአንድ ከተማ መከራ ሲያበዙባችሁ፥ ወደ ሌላው ሽሹ፤ በእውነት እላችኋለሁ የሰው ልጅ ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተሞች ሁሉ አታዳርሱም።


ከዚያን ወዲያ ኢየሱስ በአይሁድ መካከል በግልጥ አልተመላለሰም፤ ነገር ግን ከዚያ ወጥቶ በበረሓ አጠገብ ወዳለችው ኤፍሬም ወደምትባለው ከተማ ሄደ፤ እዚያ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ቈየ።


እንደገናም ኢየሱስ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሮ ዮሐንስ መጀመሪያ ያጠምቅበት ወደነበረው ስፍራ ሄደ፤ በዚያም ቈየ።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ ምድር ሄደ፤ በዚያም እያጠመቀ ከእነርሱ ጋር ለጥቂት ጊዜ ቈየ።


ኢየሱስ ይህን የተአምራት ሁሉ መጀመሪያ የሆነውን ተአምር በገሊላ ምድር በቃና ከተማ አደረገ፤ በዚህም ዐይነት ክብሩን ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።


በማግስቱ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ለመሄድ ፈለገ፤ ፊልጶስንም አገኘውና “ተከተለኝ!” አለው።


ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ገሊላ ባሕር ሄደ። ከገሊላና ከይሁዳ ብዙ ሰዎች ተከተሉት።


እርሱ ያየውንና የሰማውን ይመሰክራል፤ ነገር ግን የእርሱን ምስክርነት የሚቀበል የለም።


ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ በሰማርያና በገሊላ መካከል ያልፍ ነበር፤


እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ምድር ወደ ገሊላ መምጣቱን ሰምቶ ወደ እርሱ ሄደ፤ ወደ ቅፍርናሆም እንዲወርድና በጠና ታሞ ሊሞት የተቃረበውን ልጁን እንዲፈውስለት ኢየሱስን ለመነው።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በገሊላ ይዘዋወር ነበር፤ አይሁድ ሊገድሉት ይፈልጉ ስለ ነበረ ግን በይሁዳ ሊዘዋወር አልፈለገም፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements