Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 2:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አይሁድ የመንጻት ሥርዓት ስለ ነበራቸው ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ነበሩ፤ እያንዳንዱ ጋን ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ውሃ ለመያዝ ይችል ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በአይሁድ የመንጻት ሥርዐት መሠረት፣ ከሰባ ዐምስት እስከ አንድ መቶ ዐሥራ ዐምስት ሊትር የሚይዙ ከድንጋይ የተሠሩ ስድስት ጋኖች በዚያ ነበሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በዚ​ያም እንደ አይ​ሁድ ልማድ የሚ​ያ​ነ​ጹ​ባ​ቸው ስድ​ስት የድ​ን​ጋይ ጋኖች ነበሩ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም እያ​ን​ዳ​ንዱ ሁለት ወይም ሦስት እን​ስራ ይይዙ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 2:6
9 Cross References  

በዚያን ጊዜ በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከል ስለ መንጻት ሥርዓት ክርክር ተነሣ።


እነዚህ ነገሮች የመታደስ ጊዜ እስኪመጣ ድረስ በሥራ ላይ የዋሉ አፍአዊ ሥርዓቶች ናቸው፤ እነርሱ ስለ መብልና ስለ መጠጥ፥ ስለ ልዩ ልዩ የመንጻት ሥርዓቶችም ብቻ የተደረጉ ናቸው።


ክርስቶስ ይህን ያደረገው ቤተ ክርስቲያንን ሊቀድሳት ፈልጎ ነው፤ የቀደሳትም በቃሉ አማካይነት በውሃ አጥቦ ነው።


ስለዚህ ከክፉ ኅሊና እንድንነጻ ልባችንን ተረጭተን፥ ሰውነታችንንም በንጹሕ ውሃ ታጥበን፥ ቅን ልብና እውነተኛ እምነት ይዘን ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ።


በመጀመሪያ ሙሴ የሕጉን ትእዛዞች ለሕዝቡ ሁሉ ነገረ፤ ከዚህ በኋላ የወይፈኖችንና የፍየሎችን ደም ከውሃ ጋር አድርጎ የሕጉን መጽሐፍና ሕዝቡን ሁሉ በሂሶጵና በቀይ የበግ ጠጒር ረጨ፤


እንዲሁም የጥምቀትን፥ የእጅ መጫንን፥ ከሞት የመነሣትን፥ የዘለዓለም ፍርድን ትምህርት እንደገና አንመሥርት።


እርሱም ‘መቶ ማድጋ ዘይት ዕዳ አለብኝ’ አለ፤ መጋቢው ‘የፈረምከው ውል ይኸውልህ ቶሎ ተቀመጥና ኀምሳ ማድጋ ብለህ ጻፍ’ አለው።


ኢየሱስ አገልጋዮቹን “ጋኖቹን ውሃ ሙሉአቸው” አላቸው፤ እነርሱም እስከ አፋቸው ሞሉአቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements