ኢዩኤል 2:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እነርሱ በፊታቸው የሚገኘውን ተክል ሁሉ እንደ እሳት ይበላሉ፤ እንደ ነበልባልም ያቃጥላሉ። ገና ያልደረሱበት፥ በፊታቸው ያለው ምድር፥ እንደ ዔደን የአትክልት ቦታ የለመለመ ነው፤ እነርሱ ያለፉበት ምድር ግን የወደመ በረሓ ይሆናል፤ ከእነርሱ የሚያመልጥ ምንም ነገር አይገኝም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 በፊታቸው፣ እሳት ይባላል፤ በኋላቸውም ነበልባል ይለበልባል፤ በፊታቸው ምድሪቱ እንደ ዔድን ገነት ናት፤ በኋላቸውም የሚቀረው ባዶ ምድረ በዳ ነው፤ ምንም አያመልጣቸውም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 እሳት በፊታቸው ትባላለች፥ በኋላቸውም ነበልባል ታቃጥላለች፥ ምድሪቱ በፊታቸው እንደ ዔድን ገነት፥ በኋላቸውም የምድረ በዳ በረሃ ናት፥ ከእነርሱም የሚያመልጥ የለም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 እሳት በፊታቸው ትበላለች፥ በኋላቸውም ነበልባል ታቃጥላለች፤ ምድሪቱ በፊታቸው እንደ ደስታ ገነት፥ በኋላቸውም እንደ ምድረ በዳ በረሃ ናት፤ ከእርሱም የሚያመልጥ የለም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 እሳት በፊታቸው ትባላለች፥ በኋላቸውም ነበልባል ታቃጥላለች፥ ምድሪቱ በፊታቸው እንደ ዔድን ገነት፥ በኋላቸውም የምድረ በዳ በረሃ ናት፥ ከእነርሱም የሚያመልጥ የለም። See the chapter |