| ኤርምያስ 39:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ የክብር ዘቡ አዛዥ ናቡዛርዳን በከተማ የቀሩትን ሕዝብና ቀደም ብለው ወደ እርሱ ከድተው የገቡትንም ሁሉ በአንድነት ሰብስቦ በእስረኛነት ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤See the chapter አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 የባቢሎን መንግሥት የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ በከተማዪቱ የቀረውን ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።See the chapter መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን በከተማይቱ የቀሩትን ሕዝብ፥ ወደ እርሱም ኮብልለው የነበሩትን ሰዎች፥ የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማርኮ አፈለሳቸው።See the chapter የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳንም በከተማዪቱ የቀሩትን ሕዝብ፥ ኰብልለውም ወደ እርሱ የገቡትን ሰዎችና የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው።See the chapter መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን በከተማይቱ የቀሩትን ሕዝብ ወደ እርሱም የኰበለሉትን ሰዎች የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው።See the chapter |