Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 2:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰማያት ሆይ! ከዚህ የተነሣ ደንግጡ፤ በታላቅ ፍርሀትም ተንቀጥቀጡ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሰማያት ሆይ፤ በዚህ ተገረሙ፤ በታላቅ ድንጋጤም ተንቀጥቀጡ፤” ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሰማያት ሆይ! በዚህ ተሣቀቁ፥ እጅግም ደንግጡና ተንቀጥቀጡ ይላል ጌታ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሰማይ በዚህ ደነ​ገጠ፤ እጅ​ግም ተን​ቀ​ጠ​ቀጠ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሰማያት ሆይ፥ በዚህ ተደነቁ፥ እጅግም ደንግጡና ተንቀጥቀጡ ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 2:12
10 Cross References  

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰማያት ሆይ! ስሙ፤ ምድርም አድምጪ፤ ተንከባክቤ ያሳደግኋቸው ልጆች ዐመፀኞች ሆኑብኝ፤


እናንተ ተራራዎች! እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ የሚያቀርበውን ወቀሳ ስሙ! እናንተም ጠንካራ የሆናችሁ የምድር መሠረቶች! አድምጡ! እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን ይወቅሳል ይገሥጻልም።


ምድር፥ ምድር፥ ምድር ሆይ! እግዚአብሔር የሚለውን ቃል እነሆ አድምጪ!


ምድር ሆይ! ስሚ! እነርሱ ያስተማርኳቸውን ሥርዓት ስለ ተቃወሙ፤ ለሕጌም ስላልታዘዙ ስለ ክፉ ሐሳባቸው ሁሉ እቀጣቸው ዘንድ በሕዝቡ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ።


ሰማይ ሆይ፥ የምናገረውን አድምጥ፤ ምድርም ከአፌ የሚወጣውን ቃል ትስማ፤


ከስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ጨለማ ሆነ።


ምድርን ተመለከትኩ፤ እነሆ ባድማ ሆናለች፤ ሰማይንም ተመለከትኩ፤ እነሆ ብርሃን አይታይበትም።


እንደ ደነቈራችሁና እንደ ታወራችሁ ቅሩ! ምንም ወይን ጠጅ ሳትጠጡ የሰከራችሁ ሁኑ! ምንም ዐይነት የሚያሰክር መጠጥ ሳትቀምሱ ተንገዳገዱ!


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን የመሰለ ነገር በሕዝቦች መካከል ተሰምቶ እንደ ሆነ ጠይቁ፤ የተለዩ የእስራኤል ሕዝብ በጣም አጸያፊ የሆነ ነገር አድርገዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements