Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 8:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ደግሞም ሰባት ቀን ከቈየ በኋላ ኖኅ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት፤ በዚህን ጊዜ ግን ርግቢቱ ሳትመለስለት ቀረች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሰባት ቀንም ቈይቶ ርግቧን እንደ ገና ላካት፤ በዚህ ጊዜ ግን ርግቧ ወደ እርሱ አልተመለሰችም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ደግሞም ሰባት ቀን ከቈየ በኋላ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት፤ ዳግመኛም ወደ እርሱ ሳትመለስለት ቀረች።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ደግሞ ሰባት ቀን ቆይቶ፥ ርግ​ብን ላካት፤ ዳግ​መ​ኛም ወደ እርሱ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ደግሞ እስከ ሰባት ቀም ቆየ ርግብንም ሰደዳት ዳግመኛም ወደ እርሱ አልስተመለሰችም።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 8:12
12 Cross References  

ይህም ሁሉ ሆኖ እግዚአብሔር ምሕረት ሊያደርግላችሁ ተዘጋጅቶአል፤ እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ስለ ሆነ ሊራራላችሁ ወዶአል፤ ስለዚህ በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።”


አምላክ ሆይ፥ ሕግህን እየጠበቅን በአንተ ተስፋ እናደርጋለን። የልባችንም ምኞት የአንተ ገናናነት በሕዝቦች ዘንድ እንዲታወቅ ማድረግ ነው።


ይህም በሚፈጸምበት ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “እነሆ፥ እርሱ አምላካችን ነው፤ በእርሱ ስለ ታመንን አድኖናል፤ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ እኛም በእርሱ ታምነናል፤ እርሱ ስለ ታደገን በደስታ ተሞልተን ሐሴት እናደርጋለን!” ይላሉ።


ሰባት ቀን ከቈየም በኋላ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት።


ምንም እንኳ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ ፊቱን ቢመልስባቸውም እኔ በእርሱ ላይ እተማመናለሁ።


በእግዚአብሔር ታመን፤ በርታ፤ ተስፋ አትቊረጥ፤ በእግዚአብሔር ታመን።


ምክንያቱም ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ይጠብቃል፤ እርሱም የሚናገረው የሚፈጸምበትን ቀን ነው፤ ሐሰትም የለበትም፤ ጊዜ የሚወስድ ቢመስልም ጠብቅ፤ በእርግጥ ይደርሳል፤ አይዘገይምም።


እርስዋም ወደ ማታ ጊዜ የለመለመ የወይራ ዘይት ዛፍ ቅጠል በአፍዋ ይዛ ወደ ኖኅ ተመለሰች፤ በዚህ ሁኔታ ኖኅ ውሃው ከምድር መጒደሉን ዐወቀ።


“የሞአብ ነዋሪዎች ሆይ! ከተሞቻችሁን ለቃችሁ በገደል አፋፍ ጎጆዋን እንደምትሠራ እንደ ርግብ በመሆን በቋጥኞች መካከል ኑሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements