Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 7:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከያንዳንዱ ዐይነት ወፍ ወንድና ሴት ሰባት ወንድ ሰባት ሴት አስገባ፤ ይህንንም የምታደርገው እያንዳንዱ ዐይነት እንስሳና ወፍ በሕይወት እንዲኖርና በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፍ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እንዲሁም ከወፎች ወገን ሁሉ ሰባት ተባዕትና ሰባት እንስት፣ በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፉ ከአንተ ጋራ ታስገባለህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከን​ጹሕ የሰ​ማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባ​ትና እን​ስት፥ ንጹሕ ካል​ሆነ የሰ​ማይ ወፍም ሁለት ሁለት ተባ​ትና እን​ስት እያ​ደ​ረ​ግህ በም​ድር ላይ ለም​ግ​ብና ለዘር ይቀር ዘንድ ለአ​ንተ ትወ​ስ​ዳ​ለህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት እያደረልግልህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትውስዳለህ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 7:3
6 Cross References  

በሕይወት እንዲኖሩ ከየዐይነቱ ወፎች፥ ከየዐይነቱ እንስሶች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ከልዩ ልዩ ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች በየዐይነቱ ሁለት ሁለት ወደ አንተ ይምጡ።


ንጹሕ ከሆኑት ወንዶችና ሴቶች እንስሶች ሁሉ ሰባት ወንድ፥ ሰባት ሴት ከአንተ ጋር ወደ መርከቡ አስገባ፤ ንጹሕ ካልሆኑት ወንዶችና ሴቶች እንስሶች ሁሉ ግን፥ አንድ ወንድ አንድ ሴት አስገባ።


የፈጠርኩትን ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ገጽ ላይ ለማጥፋት ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ዝናብ አዘንባለሁ።”


ንጹሕ ከሆኑትና ካልሆኑት ከያንዳንዱ ዐይነት እንስሶች ወፎች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሁሉ


ኖኅ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ፤ ንጹሕ ከሆኑት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ከየዐይነቱ አንዳንድ ወሰደ፤ መሥዋዕት እንዲሆኑም ሁሉንም በመሠዊያው ላይ አቃጠላቸው።


እንደነዚህ ያሉት እንስሶች በእናንተ ዘንድ የረከሱ ሆነው መቈጠር አለባቸው፤ እነርሱን መብላት ቀርቶ በድናቸውን መንካት እንኳ የለባችሁም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements