Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 42:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በከነዓን ምድርም ራብ ገብቶ ስለ ነበር የያዕቆብ ልጆች ከሌሎች ሰዎች ጋር እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ሄዱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ራቡ በከነዓንም በመበርታቱ፣ እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ከሄዱት ሰዎች መካከል የእስራኤል ልጆችም ነበሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ራቡ በከነዓንም በመበርታቱ፥ እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ከሄዱት ሰዎች መካከል የእስራኤል ልጆችም ነበሩ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለእ​ህል ሸመታ ከመ​ጡት ጋር ገቡ፤ በከ​ነ​ዓን ሀገር ራብ ነበ​ርና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የእስራኤልም ልጆች ለእህል ሸመታ ከመጡቱ ጋር ገቡ በከነዓን አገር ራብ ነበረና።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 42:5
7 Cross References  

በዚያን ጊዜ በግብጽና በከነዓን አገር ሁሉ ላይ ታላቅ ችግር ያስከተለ ራብ ሆነ፤ አባቶቻችንም ምግብ ሊያገኙ አልቻሉም።


በዓለም ላይ ራብ ጸንቶ ስለ ነበር የልዩ ልዩ አገር ሕዝቦች ከዮሴፍ እህል ለመግዛት ወደ ግብጽ አገር መጡ።


በከነዓን ምድር ራብ ገባ፤ ራብም እየበረታ በመሄዱ አብራም የራቡን ጊዜ ለማሳለፍ በስተደቡብ ርቆ ወደ ግብጽ አገር ሄደ።


በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ራብ ሌላ ዳግመኛ ራብ በምድር ላይ መጣ፤ በዚህ ምክንያት ይስሐቅ የፍልስጥኤማውያን ንጉሥ አቤሜሌክ ወዳለበት ወደ ገራር ሄደ፤


ከእነርሱም አንዱ አጋቦስ የሚባለው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ እንደሚሆን በመንፈስ ቅዱስ አነሣሽነት ትንቢት ተናገረ፤ ይህም የሆነው በሮም ንጉሠ ነገሥት በቀላውዴዎስ ዘመን ነበር።


በዳዊት ዘመነ መንግሥት ሦስት ዓመት ሙሉ ጽኑ ራብ ነበር፤ ዳዊትም ስለዚህ ጉዳይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በጠየቀ ጊዜ እግዚአብሔር “ሳኦልና ቤተሰቡ ግድያ በመፈጸም በደል ሠርተዋል፤ ሳኦልም የገባዖንን ሰዎች ፈጅቶአል” ሲል መለሰለት።


ዮሴፍ አስቀድሞ እንደ ተናገረው፥ ሰባቱ የራብ ዓመቶች መግባት ጀመሩ፤ በሌሎች አገሮች ሁሉ ራብ ሆነ፤ ይሁን እንጂ በመላው የግብጽ ምድር በቂ ምግብ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements