Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 41:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ሰባቱ የሚያምሩ ላሞች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ ሰባቱም ያማሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ የሁለቱም ትርጒም አንድ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ሰባቱ የሚያማምሩ ላሞች፣ ሰባት ዓመታት ናቸው፣ ሰባቱም የሚያማምሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሕልሙም አንድና ተመሳሳይ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሰባቱ የሚያማምሩ ላሞች፥ ሰባት ዓመታት ናቸው፥ ሰባቱም የሚያማምሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሕልሙም አንድና ተመሳሳይ ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እነ​ዚያ ሰባቱ መል​ካ​ካ​ሞች ላሞች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ እነ​ዚ​ያም ሰባቱ መል​ካ​ካ​ሞች እሸ​ቶች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ የፈ​ር​ዖን ሕልሙ አንድ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ሰባቱ መልካካሞች ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፥ ሰባቱም መልካካሞች እሸቶች ሰባት ዓመታት ናቸው ሕልሙ አንድ ነው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 41:26
15 Cross References  

በሰባቱ የጥጋብ ዓመቶች ምድሪቱ እጅግ ብዙ ሰብል ሰጠች።


ሰባት የወፈሩና የሰቡ ላሞች ከወንዙ ወጥተው ሣር ሲበሉ አየ፤


ሦስት ምስክሮች አሉ፤


ሁሉም አንድ ዐይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ የጠጡትም ይከተላቸው ከነበረው ከዚያ ከመንፈሳዊ አለት የመነጨ ነበር፤ ያም አለት ራሱ ክርስቶስ ነበር።


ለጒዞ እንደ ተዘጋጀ ሰው ሆናችሁ ወገባችሁን በመታጠቅ ጫማችሁን አድርጋችሁ፥ በትራችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ በችኰላ ብሉት፤ እርሱም እኔን እግዚአብሔርን የምታከብሩበት የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ።


በግብጽ ምድር ጥጋብ የበዛባቸው ሰባቱ ዓመቶች ተፈጸሙ፤


በመላው የግብጽ ምድር ላይ ታላቅ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመቶች ይመጣሉ።


ተመልሶም እንቅልፍ በወሰደው ጊዜ እንደገና ሌላ ሕልም አየ፤ በሕልሙም በአንድ የእህል አገዳ ላይ ሰባት የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች አየ፤


ዮሴፍም “የሕልሙ ትርጒም እንዲህ ነው፤ ሦስት መሶቦች ሦስት ቀኖች ናቸው፤


ዮሴፍም እንዲህ አለ፤ “የሕልሙ ትርጕም ይህ ነው፤ ሦስቱ የወይን ሐረጎች ሦስት ቀኖች ናቸው፤


ስለዚህ ወንድ አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይተባበራል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ።


የተቀደሰው ድንኳን አንድ ይሆን ዘንድ ለእነዚህ ሁለት ክፍሎች ኀምሳ የወርቅ መያዣዎችን ሠርተህ በቀለበቶቹ አገጣጥማቸው።።


ዮሴፍም ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ “የሁለቱም ሕልሞችህ ትርጒም አንድ ነው፤ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ነገር አስቀድሞ ገልጦልሃል፤


ከእነርሱም በኋላ የወጡት ሰባት የከሱትና አስከፊዎቹ ላሞች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ እንዲሁም ሰባቱ የቀጨጩና በበረሓ ነፋስ ተመተው የሰለቱ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ የሁለቱም ትርጒም አንድ ነው፤ ይኸውም ሰባት የራብ ዓመቶች ናቸው።


የሰው እጅ ሳይነካው ከተራራ ላይ ተፈንቅሎ በመውረድ ከብረት፥ ከነሐስ፥ ከሸክላ፥ ከብርና ከወርቅ የተሠራውን ምስል ያደቀቀውም ድንጋይ፥ ያ መንግሥት ነው፤ በዚህም ታላቁ አምላክ ወደፊት የሚሆነውን ሁሉ አሳይቶሃል፤ እነሆ፥ ሕልሙ እውነት ነው፤ አስተማማኝ ትርጒሙም ይኸው ነው።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements