Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 4:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እግዚአብሔርም ቃየልን “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” ሲል ጠየቀው፤ ቃየልም “የት እንዳለ አላውቅም፤ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” ብሎ መለሰ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም፣ እግዚአብሔር ቃየንን፣ “ወንድምህ አቤል የት ነው?” አለው። ቃየንም፣ “አላውቅም፤ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” ሲል መለሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ጌታም ቃየንን፥ “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” አለው። እርሱም፥ “አላውቅም፥ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ?” አለ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃየ​ልን አለው፥ “ወን​ድ​ምህ አቤል ወዴት ነው?” ቃየ​ልም አለ፥ “አላ​ው​ቅም፤ በውኑ የወ​ን​ድሜ ጠባ​ቂው እኔ ነኝን?”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እግዚአብሔርም ቃየንን አለው፤ ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ፤ አላውቅም የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን? አለውም፤

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 4:9
11 Cross References  

ኃጢአቱን የሚደብቅ ኑሮው አይሳካለትም፤ ኃጢአቱን ተናዝዞ ዳግመኛ ኃጢአት ከመሥራት የሚቈጠብ ግን የእግዚአብሔርን ምሕረት ያገኛል።


እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ልጆች ናችሁ፤ ፍላጎታችሁም የአባታችሁን ምኞት መፈጸም ነው፤ እርሱ ከመጀመሪያ አንሥቶ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነት በእርሱ ስለሌለ ከእውነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ እርሱ ሐሰተኛና የሐሰት ሁሉ አባት ስለ ሆነ ሐሰት በሚናገርበት ጊዜ ከገዛ ራሱ አውጥቶ ይናገራል።


እግዚአብሔር የተጨቈኑትን ያስታውሳል ጩኸታቸውን አይረሳም የሚበድሉአቸውንም ይቀጣል።


ብዙ ኅብር ያለበትንም ልብሱን ወደ አባታቸው ወስደው “እነሆ፥ ይህን አገኘን የልጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ እይ” አሉት።


እግዚአብሔርም ቃየልን እንዲህ አለው፤ “ምን አደረግህ? የፈሰሰው የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ እየጮኸ ነው፤


በዚህ ጊዜ ይሁዳ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “ወንድማችንን ገድለን የአሟሟቱን ሁኔታ ብንደብቅ ምን ይጠቅመናል?


እግዚአብሔር ሆይ! ምሕረትን አድርግልኝ! ጠላቶቼ የሚያደርሱብኝን መከራ ተመልከት! ከሞትም አድነኝ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements