ዘፍጥረት 39:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ይህም ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር በዮሴፍ ምክንያት የግብጻዊውን ሰው ቤት ንብረትና በውጪም በእርሻ ያለውን ሀብት ሁሉ ባረከለት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ፣ እግዚአብሔር የግብጻዊውን ቤት ባረከ፤ የእግዚአብሔርም በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ ጌታ የግብፃዊውን ቤት ባረከ፥ የጌታም በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 እንዲህም ሆነ፤ በቤቱ ባለውም ሁሉ ላይ ከሾመው በኋላ እግዚአብሔር የግብፃዊውን ቤት በዮሴፍ ምክንያት ባረከው። የእግዚአብሔርም በረከት በቤቱም፥ በእርሻውም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 እንዲህም ሆነ በቤቱ ባለውም ሁሉ ላይ ከሾመው በኍላ እግዚአብሔር የግብፃዊውን ቤት ስለ ዮሴፍ ባረከው የእግዚአብሔር በረከት በውጪም በግቢም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ። See the chapter |