Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 38:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ስለ ነበረ፥ እግዚአብሔር በሞት ቀሠፈው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የይሁዳ የበኵር ልጅ ዔር ግን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የይሁዳ የበኩር ልጅ ዔር ግን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር፤ ጌታም ቀሠፈው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የይ​ሁ​ዳም የበ​ኵር ልጅ ዔር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀሠ​ፈው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የይሁዳም የበኵር ልጅ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ እግዚአብሔር ቀሠፈው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 38:7
11 Cross References  

ይሁዳ ከከነዓናዊት ሚስቱ ከባትሹዓ ዔር፥ ኦናንና ሼላ ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ የበኲር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ስለ ነበር እግዚአብሔር በሞት ስለ ቀሠፈው፥


የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፥ ኦናን፥ ሴላ፥ ፋሬስና ዛራሕ ናቸው፤ ዔርና ኦናን ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል። የፋሬስ ልጆች ሔጽሮንና ሐሙል ናቸው።


የይሁዳ ነገድ ተወላጆች፥ ኤርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ።


ይህችን ከተማ ልናጠፋት ነው፤ የእነዚህ ሰዎች ኃጢአት እጅግ መብዛቱን እግዚአብሔር ሰምቶአል፤ ሰዶምንም እንድናጠፋ ልኮናል።”


በዚያን ዘመን የሰዶም ሰዎች እጅግ ክፉዎችና እግዚአብሔርን የሚያሳዝኑ ኃጢአተኞች ነበሩ።


አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።


የገዛ ወንዶች ልጆቹንም በሂኖም ሸለቆ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እርሱም ራሱ ሟርተኛና አስማተኛ ሆኖ፥ ከጠንቋዮችና ከሙታን ጠሪዎች ምክርን ይጠይቅ ነበር፤ በዚህም ሁሉ አድራጎቱ ታላቅ ኃጢአት ስለ ሠራ፥ እግዚአብሔርን አስቈጣ።


ይሁን እንጂ ኖኅ የተባለው ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን አግኝቶ ነበር።


ይሁዳ የመጀመሪያ ልጁን ዔርን ትዕማር ከምትባል ልጃገረድ ጋር አጋባው።


አንድ ሰው ሌላውን ሰው ቢበድል፥ እግዚአብሔር በመታደግ ሊያድነው ይችላል፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚበድል ሰው ማን ሊያማልደው ይችላል?” ሆኖም እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ቊርጥ ውሳኔ ስላደረገ የዔሊ ልጆች የአባታቸውን ምክር አልሰሙም።


ከዚህ በኋላ ኤልያስ ድምፁን ከፍ በማድረግ “እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ስለምን በዚህች ባልዋ በሞተባት ሴት ላይ ይህን የመሰለ አሠቃቂ ነገር አደረግህ? እርስዋ እኔን በማስተናገድ ታላቅ ቸርነት አድርጋልኛለች፤ ታዲያ አንተ ስለምን ልጅዋ እንዲሞት አደረግህ?” ሲል ጸለየ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements