Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 38:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከዚህ በኋላ ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን “ልጄ ሴላ እስከሚያድግበት ጊዜ ድረስ ሂጂና በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ኑሪ” አላት። ይህንንም ያለው እንደ ወንድሞቹ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሰጋ ነበር፤ ስለዚህ ትዕማር ሄዳ በአባቷ ቤት ተቀመጠች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፣ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት። ይህን ያለውም፣ ሴሎም እንደ ወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሠጋ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፥ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት፤ ይህን ያለውም፥ ሴሎም እንደ ወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሠጋ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ይሁ​ዳም ምራ​ቱን ትዕ​ማ​ርን፥ “ልጄ ሴሎም እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በአ​ባ​ትሽ ቤት መበ​ለት ሆነሽ ተቀ​መጪ” አላት፤ እርሱ ደግሞ እንደ ወን​ድ​ሞቹ እን​ዳ​ይ​ሞ​ት​ብኝ ብሎ​አ​ልና። ትዕ​ማ​ርም ሄዳ በአ​ባቷ ቤት ተቀ​መ​ጠች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ይሁዳም ምራትን ትዕማርን፦ ልጄ ሴሎም እስኪያድግ ድረስ በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ተቀመጪ አላት እርሱ ደግሞ እንደ ወንድሞቹ እንዳይሞት ብሎአልና። ትዕማርም ሄዳ በአባትዋ ቤት ተቀመጠች።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 38:11
3 Cross References  

ነገር ግን ልጅ ሳትወልድ ባልዋ የሞተባት ወይም ከባልዋ በመፋታት ወደ አባቷ ቤት ተመልሳ መጥታ በጥገኝነት የምትኖር የካህኑ ልጅ በልጅነትዋ ታደርገው እንደ ነበረው ሁሉ የአባቷ ድርሻ ከሆነው ቅዱስ ነገር ትብላ፤ ሆኖም ከካህኑ ቤተሰብ ሌላ ሰው የተቀደሰውን ነገር መብላት የለበትም።


ስለዚህ ትዕማር የመበለትነት ልብሷን ለውጣ ፊቷን በሻሽ ሸፈነች፤ ወደ ቲምና በሚወስደው መንገድ ዳር በዔናይም ደጅ ተቀመጠች፤ ይህንንም ያደረገችው ሴላ አድጎ ሳለ ለእርሱ በሚስትነት እንድትሰጥ አለመፈቀዱን ስለ ተረዳች ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements