Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 30:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እርስዋም “እነሆ፥ አገልጋዬ ባላ እዚህ አለች፤ በእኔ ምትክ ልጅ እንድትወልድልኝ ወደ እርስዋ ግባ፤ በዚህ ዐይነት በእርስዋ አማካይነት የልጆች እናት እሆናለሁ” አለችው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እርሷም፣ “እነሆ፤ አገልጋዬ ባላ አለችልህ፤ ልጆች እንድትወልድልኝና እኔም ደግሞ በርሷ አማካይነት ልጆች እንዳገኝ ከርሷ ጋራ ተኛ” አለችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እርሷም ባርያዬ ባላ እነሆ አለች፥ ድረስባት፥ በእኔም ጭን ላይ ትውለድ፥ የእርሷም ልጆች ለእኔ ደግሞ ይሁኑልኝ አለች።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እር​ስ​ዋም፥ “ባሪ​ያዬ ባላ እነሆ አለች፤ ወደ እር​ስዋ ግባ፤ በእ​ኔም ጭን ላይ ትው​ለድ፤ የእ​ር​ስ​ዋም ልጆች ለእኔ ደግሞ ይሁ​ኑ​ልኝ” አለች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እርስዋምም ባሪያዬ ባላ እነሆ አለች፤ ድረስባት፤ በእኔም ጭን ላይ ትውለድ፥ የእርስዋም ልጆች ለእኔ ደግሞ ይሁኑልኝ አለች።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 30:3
6 Cross References  

የኤፍሬምንም ልጆችና የልጅ ልጆች እስከሚያይ ድረስ ቈየ፤ ከምናሴ የተወለደውንም የማኪርንም ልጆች እንደ ልጆቹ አድርጎ ተቀበላቸው።


ጒልበቶች እኔን ለመቀበል፥ ጡቶችም እኔን ያጠቡ ዘንድ ለምን ተገኙ?


በአደባባይ ተቀምጠው የነበሩት ሽማግሌዎችና ሌሎችም ሰዎች እንዲህ አሉ፥ “አዎ፥ እኛ ለዚህ ነገር ምስክሮች ነን፤ እግዚአብሔር ይህችን ሚስትህን ብዙ ልጆችን በመውለድ የያዕቆብን ቤት እንደ መሠረቱት እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርግልህ፤ እግዚአብሔር በኤፍራታ ያበልጽግህ፤ በቤተልሔምም ዝነኛ ያድርግህ፤


ልያም መውለድ እንዳቆመች በተገነዘበች ጊዜ አገልጋይዋን ዚልፋን እንደ ሚስት አድርጋ ለያዕቆብ ሰጠችው፤


እነዚህ ሰባቱ ላባ ለልጁ ለራሔል ከሰጣት ከባላ የተወለዱ የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements