| ዘፍጥረት 28:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ስለዚህ ከዚህ በፊት ካገባቸው ሌላ በተጨማሪ ወደ አብርሃም ልጅ ወደ እስማኤል ሄዶ ልጁን ማሕላትን አገባ፤ እርስዋም የነባዮት እኅት ናት።See the chapter አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ስለዚህም ወደ እስማኤል ሄደ፣ የአብርሃም ልጅ እስማኤል የወለዳትን፣ የነባዮትን እኅት ማዕሌትን በሚስቶቹ ላይ ተጨማሪ አድርጎ አገባ።See the chapter መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ዔሳው ወደ እስማኤል ሄደ፥ ማዕሌትንም በፊት ካሉት ሚስቶቹ ጋር ሚስት ትሆነው ዘንድ አገባ፥ እርሷም የአብርሃም ልጅ የሆነ የእስማኤል ልጅና የነባዮት እኅት ናት።See the chapter የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ዔሳው ወደ ይስማኤል ሄደ፤ ቤሴሞትንም በፊት ካሉ ሚስቶቹ ጋር ሚስት ትሆነው ዘንድ ወሰዳት፤ እርስዋም የናኮር ወንድም የአብርሃም ልጅ የሆነው የይስማኤል ልጅና የናቡዓት እኅት ናት።See the chapter መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ዔሳው ወደ እስማኤል ሄደ ማዕሌትንም በፊት ካሉት ሚስቶች ጋር ሚስት ትሆነው ዘንድ አገባ እርስዋም የአብርሃም ልጅ የሆነ የእስማኤል ልጅና የነባዮት እኅት ናት።See the chapter |