Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 27:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ዔሳው ይህን በሰማ ጊዜ ድምፁን ከፍ በማድረግ ምርር ብሎ እያለቀሰ “አባቴ ሆይ! እኔንም መርቀኝ!” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ዔሳው የአባቱን ቃል ሲሰማ፣ ድምፁን ከፍ በማድረግ ምርር ብሎ አለቀሰ፤ አባቱንም፣ “አባቴ ሆይ፤ እኔንም ደግሞ እባክህ መርቀኝ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ዔሳውም የአባቱን ቃል በሰማ ጊዜ ታላቅ እጅግም መራራ ጩኸት ጮኸ፥ አባቱንም፦ “አባቴ ሆይ፥ እኔንም ደግሞ ባርከኝ” አለው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ዔሳ​ውም የአ​ባ​ቱን ቃል በሰማ ጊዜ ታላቅ፥ እጅ​ግም መራራ ጩኸት ጮኸ፤ አባ​ቱ​ንም፥ “አባቴ ሆይ፥ እኔ​ንም ደግሞ ባር​ከኝ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ዔሳውም የአባቱን ቃል በሰማ ጊዜ ታላቅ እጅግም መራራ ጩኸት ጮኸ አባቱንም፦ አባቴ ሆይ እኔንም ደግሚ ባርከኝ አለው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 27:34
8 Cross References  

በኋላም ዔሳው በረከትን እንደገና ለመቀበል በፈለገ ጊዜ ይህን በረከት እንደ ተከለከለ ታውቃላችሁ፤ እያለቀሰ እንኳ ያንን በረከት ተግቶ ቢፈልግ ሊያገኘው አልቻለም። ለንስሓ ምንም ዕድል አላገኘም።


ስለዚህ የሚገባችሁን ቅጣት ትቀበላላችሁ፤ የተንኰላችሁንም ውጤት ታገኛላችሁ።


ዳዊትና ተከታዮቹም ፈጽሞ እስኪደክሙ ድረስ ባለማቋረጥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ።


አንድ ሰው በሞኝነቱ ጥፋት ሲደርስበት በእግዚአብሔር ላይ ያማርራል።


ይስሐቅም “ወንድምህ መጥቶ እኔን በማታለል የአንተን ምርቃት ወስዶብሃል” አለው።


መርዶክዮስም ስለ ተደረገው ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ ከዚህም በኋላ ማቅ ለብሶና በራሱ ላይ ዐመድ ነስንሶ ድምፁን ከፍ አድርጎ እየጮኸ በመረረ ሁኔታ በማልቀስ ወደ ከተማይቱ ውስጥ ገባ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements