Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 27:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ይስሐቅ ያዕቆብን መርቆ እንዳበቃና ያዕቆብም ከአባቱ ፊት እንደ ወጣ ወዲያው ወንድሙ ዔሳው ከአደን ተመልሶ መጣ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ይሥሐቅ ያዕቆብን መርቆ እንዳበቃ፣ ያዕቆብ ገና ከአባቱ ዘንድ ሳይወጣ ወዲያውኑ፣ ወንድሙ ዔሳው ከዐደን ተመለሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ይስሐቅም ያዕቆብን ባርኮ ከፈጸመ በኋላ፥ ያዕቆብም ከአባቱ ከይስሐቅ ፊት ከወጣ በኋላ፥ ወዲያው በዚያው ጊዜ ዔሳው ከአደኑ መጥቶ ገባ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ይስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብን ባርኮ ከፈ​ጸመ በኋላ፥ ያዕ​ቆብ ከአ​ባቱ ከይ​ስ​ሐቅ ፊት ወጣ፥ ወን​ድሙ ዔሳ​ውም ከአ​ደኑ መጣ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ይስሐቅም ያዕቆብን ባርኮ ከፈጸመ በኍላ ያዕቆብም ከአባቱ ለይስሕቅ ፊት ከወጣ በኍላ ወዲያው በዚያው ጊዜ ዔሳው ከአደኑ መጥቶ ገባ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 27:30
4 Cross References  

በኋላም ዔሳው በረከትን እንደገና ለመቀበል በፈለገ ጊዜ ይህን በረከት እንደ ተከለከለ ታውቃላችሁ፤ እያለቀሰ እንኳ ያንን በረከት ተግቶ ቢፈልግ ሊያገኘው አልቻለም። ለንስሓ ምንም ዕድል አላገኘም።


መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችም ያገልግሉህ፤ በወንድሞችህ ሁሉ ላይ አለቃ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚመርቁህም የተመረቁ ይሁኑ።”


እርሱም በበኩሉ የጣፈጠ ወጥ ሠርቶ ለአባቱ አቀረበለትና “አባቴ ሆይ፥ እንድትመርቀኝ፥ እስቲ ቀና ብለህ ካመጣሁልህ የአደን ሥጋ ብላ” አለው።


ናምሩድ በእግዚአብሔር ድጋፍ ታላቅ አዳኝ ነበረ፤ ሰዎች “እንደ ናምሩድ ታላቅ አዳኝ ያድርግህ!” እያሉ የሚመርቁት ስለዚህ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements