ዘፍጥረት 2:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 በዚያም ለዐይን የሚያስደስቱና ለምግብነት የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ዛፎች እንዲበቅሉ አደረገ፤ ደግሞም በአትክልቱ ቦታ መካከል ሕይወት የሚሰጥ ዛፍ ነበረ፤ እንዲሁም ደጉን ከክፉ ለመለየት የሚያስችል ዕውቀት የሚሰጥ ሌላ ዛፍ ነበረ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 እግዚአብሔር አምላክም ለዐይን የሚያስደስት ለመብልም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በአትክልቱ ቦታ መካከልም የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ እንዲሁም መልካምና ክፉን መለየት የሚያስችለው የዕውቀት ዛፍ ነበረ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 በዚያም፥ ጌታ እግዚአብሔር ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፥ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ደግሞ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያሳየውንና የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያስኘውን፤ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፤ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ። See the chapter |