ዘፍጥረት 19:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ነገር ግን ወደ ቤቱ እንዲገቡ አጥብቆ ስለ ለመናቸው፥ ከእርሱ ጋር ወደ ቤቱ ገቡ፤ ከዚህም በኋላ ሎጥ እንጀራ ጋግረው መልካም ራት እንዲያዘጋጁ ለአገልጋዮቹ ነገራቸው፤ ራትም በተዘጋጀ ጊዜ እንግዶቹ በሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ሎጥ ግን አጥብቆ ስለ ለመናቸው ዐብረውት ወደ ቤቱ ገቡ፤ ከዚያም ቂጣ ጋግሮ አቀረበላቸውና በሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 እጅግም ዘበዘባቸው፥ ወደ እርሱም አቀኑ፥ ወደ ቤቱም ገቡ፥ ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ እነርሱም በሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 እርሱም ግድ አላቸው፤ ወደ እርሱም አቀኑ፤ ወደ ቤቱም ገቡ፤ ቂጣንም አስጋገረላቸው፤ እነርሱም በሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 እጅግም ዘበዝባቸው ወደ እርሱም አቀኑ ወደ ቤቱም ገቡ፤ ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ እነርሱም በሉ። See the chapter |