Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 10:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የካም ልጆች፦ ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥና ከነዓን ናቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የካም ልጆች፦ ኵሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን ናቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የካም ልጆች፦ ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ እና ከነዓን ናቸው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የካ​ምም ልጆች ኩሽ፥ ምስ​ራ​ይም፥ ፉጥ፥ ከነ​ዓን ናቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፋጥ፥ ከነዓን ናቸው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 10:6
15 Cross References  

“ከፋርስ፥ ከልድያና ከሊቢያ የመጡ ወታደሮች በሠራዊትሽ ውስጥ ያገለግላሉ፤ ጋሻቸውንና የራስ ቊራቸውን በጦር ሰፈርሽ ሰቅለዋል፤ እነርሱ ለአንቺ ክብር ያስገኙ ሰዎች ናቸው።


ፈረሶች ወደ ፊት እንዲሄዱ፥ ሠረገሎችም አስደንጋጭ በሆነ ፍጥነት እንዲሽከረከሩ እዘዙ፤ ከኢትዮጵያና ከሊቢያ ጋሻቸውን አንግበው በመጡ ሰዎችና፥ ከልድያ በመጡ ቀስት በሚወረውሩ ኀያላን ሰዎች ጭምር የተጠናከሩ ወታደሮችን ላኩ” ይላል እግዚአብሔር።


በዚያን ጊዜ ጌታ እንደገና የኀይል ሥራ ይሠራል፤ ይኸውም በአሦር፥ በግብጽ፥ በጳጥሮስ አገሮች፥ በኢትዮጵያ፥ በዔላም፥ በባቢሎንና በሐማት እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አገሮችና በደሴቶች ሁሉ የሚኖሩትን የቀሩት ወገኖቹን ወደ አገራቸው ይመልሳቸዋል።


በዚያ ሳሉ ያደረገላቸውን አስደናቂ ነገሮችና፥ በቀይ ባሕርም ያደረገላቸውን አስገራሚ ነገሮች ዘነጉ።


እነርሱ በግብጽ ምድር የእግዚአብሔርን ድንቅ ነገሮችና ተአምራትን አደረጉ።


ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ወደ ግብጽ ሄደ፤ በዚያም አገር ስደተኛ ሆኖ ኖረ።


የካምን ልጆች የመጀመሪያ የወንድነት ፍሬ፥ በግብጽ በኲሮችን ሁሉ ገደለ።


በዚያም ጸጥታና ሰላም በሰፈነበት ገላጣማ አገር ለም የሆነ የግጦሽ ቦታ በብዛት አገኙ፤ ቀደም ሲል በዚያ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች ከካም ዘሮች ነበሩ።


የከነዓን አባት የሆነው ካም፥ አባቱ ኖኅ እራቁቱን እንደ ሆነ ባየ ጊዜ ወደ ውጪ ወጥቶ፥ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው።


ከመርከቡ የወጡት የኖኅ ልጆች ሴም፥ ካምና ያፌት ናቸው፤ ካም የከነዓን አባት ነው፤


እነዚህ ሁሉ በባሕር ዳርቻና በደሴቶች ላይ ለሚኖሩ የያፌት ዘሮች ቅድመ አያቶች ናቸው፤ በየአገራቸውና በየጐሣቸውም ተከፋፍለው የሚኖሩ ሕዝቦች ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገርበት የራሱ ቋንቋ ነበረው።


ከፋርስ፥ ከኢትዮጵያና ከሊቢያ የመጡ ሰዎችም ሁሉ ጋሻ አንግበው የራስ ቊር ደፍተው የእርሱ ተባባሪዎች በመሆን ከእርሱ ጋር ተሰልፈዋል።


ሁለተኛው ወንዝ ግዮን ይባላል፤ እርሱም ኢትዮጵያ በምትባል አገር ዙሪያ ይፈስሳል።


ኖኅ 500 ዓመት ከሆነው በኋላ ሦስት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ እነርሱም ሴም፥ ካምና ያፌት ይባሉ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements