Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 27:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራችሁ አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ ታላላቅ የሆኑ ጥቂት ድንጋዮችን አቁመህ በኖራ ለስነው፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፣ ጥቂት ትልልቅ ድንጋዮችን አቁምና በኖራ ቅባቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ጌታ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፥ ጥቂት ትልልቅ ድንጋዮችን አቁምና በኖራም ምረጋቸው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ ታላ​ላቅ ድን​ጋ​ዮ​ችን ለእ​ና​ንተ አቁሙ፤ በኖ​ራም ምረ​ጓ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ዮርዳኖስን በተሻገርህ ጊዜ ታላላቅ ድንጋዮችን ለአንተ አቁም፥ በኖራም ምረጋቸው።

See the chapter Copy




ዘዳግም 27:2
16 Cross References  

አዲስ ልብ እሰጣችኋለሁ፤ አዲስ መንፈስንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ ከሰውነታችሁ እንደ ድንጋይ የጠጠረ ልብን አውጥቼ እንደ ሥጋ የለሰለሰ ልብን እሰጣችኋለሁ።


አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ አዲስ መንፈስንም በውስጣቸው አኖራለሁ፤ ከሰውነታቸው እንደ ድንጋይ የጠጠረ ልብን አውጥቼ እንደ ሥጋ የለሰለሰ ልብን እሰጣቸዋለሁ።


የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እስራኤላውያንን ባዘዘው መሠረት በሙሴ አማካይነት በተሰጠው የሕግ መጽሐፍ ውስጥ እንደ ተጻፈው ባልተጠረበና ብረት ባልነካው ድንጋይ መሠዊያ ሠርተው የሚቃጠል መሥዋዕትና የአንድነት ቊርባን አቀረቡ።


የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ዮርዳኖስን ከተሻገሩ በኋላ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፦


“ወደ ሰፈር ሄዳችሁ ለሕዝቡ እንዲህ ብላችሁ ንገሩ፦ ‘እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትወርሱአት የሚሰጣችሁን ምድር ለመውረስ ከሦስት ቀን በኋላ ዮርዳኖስን ስለምትሻገሩ ስንቃችሁን አዘጋጁ።’ ”


የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር በማርና በወተት የበለጸገችውን ምድር እንደሚሰጥህ ቃል በገባልህ መሠረት ምድሪቱን ለመያዝ በተሻገርህ ጊዜ የዚህን ሕግ ቃሎች በድንጋዮቹ ላይ ጻፍ፤


“እግዚአብሔር አምላክህ እንድትወርሳት ወደሚሰጥህ ምድር ገብተህ በምትወርሳትና ተደላድለህ በምትቀመጥባት ጊዜ፥


አምላካችሁ እግዚአብሔር እንድትኖሩባት የሰጣችሁን ምድር ለመውረስ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁና ወርሳችሁም በምትኖሩባት ጊዜ፥


“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! አድምጥ፤ ከአንተ የሚበልጡትንና በኀይልም ብርቱ የሆኑትን የአሕዛብ ምድርና ቅጽሮቻቸው እስከ ሰማይ የደረሱ ታላላቅ ከተሞቻቸውን ለመውረስ ትገባ ዘንድ ዛሬ ዮርዳኖስን ትሻገራለህ።


“አሁን ተሻግራችሁ በርስትነት በሚሰጣችሁ ምድር እንድትጠብቁት እግዚአብሔር አምላክህ እንዳስተምርህ ያዘዘኝ ትእዛዞች፥ ሕግና ሥርዓት እነዚህ ናቸው።


ከዚህም በኋላ ሙሴ ከእስራኤል መሪዎች ጋር ሆኖ ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “ዛሬ የምሰጣችሁን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ፤


ዮርዳኖስን በተሻገርህ ጊዜ እኔ ዛሬ ባዘዝኩህ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በዔባል ተራራ ላይ አቁመህ በኖራ ለስናቸው፤


ከዚህም በኋላ ኢያሱ በዔባል ተራራ ላይ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤


ሙሴ ጽፎት የነበረውን የኦሪትን ሕግ ኢያሱ በእስራኤላውያን ፊት በድንጋይ ላይ ጻፈው።


ምነው በብረት መሣሪያና በእርሳስ ተጽፈው ወይም በድንጋይ ላይ ተቀርጸው ለዘለዓለም እንዲኖሩ ቢደረግ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር!


Follow us:

Advertisements


Advertisements