Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 22:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ነገር ግን ባለቤቱ የሚኖርበት ቦታ ሩቅ ቢሆን፥ ወይም ባለቤቱ ማን እንደ ሆነ ካላወቅህ እንስሳውን ወደ ቤትህ ውሰደው፤ እርሱን ሊፈልግ በሚመጣበት ጊዜ ለባለቤቱ ስጠው፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ወንድምህ በአቅራቢያህ ባይኖር፣ ወይም የማን መሆኑን የማታውቅ ከሆነ፣ ባለቤቱ ፈልጎት እስኪመጣ ድረስ፣ ወደ ቤትህ ወስደህ ከአንተ ዘንድ አቈየው፤ ከዚያም መልሰህ ስጠው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ወንድምህም በአቅራቢያህ ባይሆን ወይም ባታውቀው ይዘህ ወደ ቤትህ ትገባለህ፥ ወንድምህ እስኪፈልገው ድረስ በአንተ ዘንድ ይቀመጣል፥ ለእርሱም ትመልሰዋለህ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ወን​ድ​ም​ህም በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያህ ባይ​ሆን ወይም ባታ​ው​ቀው ይዘ​ሃ​ቸው ወደ ቤትህ ትገ​ባ​ለህ፤ ወን​ድ​ምህ እስ​ኪ​ሻ​ቸው ድረስ በአ​ንተ ዘንድ ይቀ​መ​ጣሉ፤ ለእ​ር​ሱም ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ወንድምህም በአቅራቢያህ ባይሆን ወይም ባታውቀው ይዘህ ወደ ቤትህ ትገባለህ፤ ወንድምህ እስኪሻው ድረስ በአንተ ዘንድ ይቀመጣል፥ ለእርሱም ትመልሰዋለህ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 22:2
4 Cross References  

በዚህ ነገር ማንም ሰው አይተላለፍ፤ ሌላ አማኝን አይበድል፤ ከዚህ በፊት እንደ ነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉትን ጌታ ይቀጣቸዋል።


እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ፥ እናንተም ለእነርሱ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የሕግና የነቢያት ትምህርትም የሚሉት ይህንኑ ነው።


“የእስራኤላዊ ወገንህ ንብረት የሆነ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ብታገኝ ዝም ብለህ አትለፈው፤ ወደ ባለቤቱ መልሰህ ውሰድለት፤


እንዲሁም አህያም ሆነ ልብስ ወይም ማንኛውንም ሌላ ነገር ከእስራኤላዊ ወገንህ ጠፍቶ ብታገኝ ችላ ሳትል መልሰህ ስጠው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements