ዘዳግም 2:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዝ፤ ዘመዶቻችሁ የዔሳው ዘሮች በሚኖሩበት በኮረብታማው በኤዶም አገር በኩል ታልፋላችሁ፤ እነርሱ እናንተን ይፈሩአችኋል፤ ነገር ግን ተጠንቀቁ፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ለሕዝቡም እነዚህን ትእዛዞች ስጣቸው፤ ‘ሴይር በሚኖሩት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ዘሮች ግዛት ዐልፋችሁ ትሄዳላችሁ፤ እነርሱ ይፈሯችኋል፤ ቢሆንም ከፍ ያለ ጥንቃቄ አድርጉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር ላይ በተቀመጡት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች አገር ታልፋላችሁ፥ እነርሱም ይፈሩአችኋል፤ እንግዲህ እጅግ ተጠንቀቁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር ላይ በተቀመጡት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች ሀገር ታልፋላችሁ፤ እነርሱ ይፈሩአችኋል፤ እንግዲህ እጅግ ተጠንቀቁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር ላይ በተቀመጡት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች አገር ታልፋላችሁ፥ እነርሱም ይፈሩአችኋል፤ እንግዲህ እጅግ ተጠንቀቁ። See the chapter |