Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 15:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ለውጪ አገር ሰው ያበደርከው ብድር እንዲመለስልህ መጠየቅ ትችላለህ፤ ለማንኛውም እስራኤላዊ ወገንህ ያበደርከው ገንዘብ ግን እንዲመለስልህ መጠየቅ የለብህም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ለባዕድ ያበደርኸውን መጠየቅ ትችላለህ፤ ወንድምህ ከአንተ የተበደረውን ማንኛውንም ዕዳ ግን ተወው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ለባዕድ ያበደርከውን መጠየቅ ትችላለህ፤ ወንድምህ ከአንተ የተበደረውን ማናቸውንም ዕዳ ግን ተወው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከባ​ዕድ ግን በእ​ርሱ ዘንድ ያለ​ህን ሁሉ መቀ​በል ትች​ላ​ለህ፤ በወ​ን​ድ​ምህ ላይ ያለ​ውን ሁሉ ግን ተው​ለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከእንግዳ ላይ ያበደርኸውን መፈለግ ትችላለህ፤ በወንድምህ ላይ ያለውን ሁሉ ግን እጅህ ይተወዋል።

See the chapter Copy




ዘዳግም 15:3
8 Cross References  

ወለድ መጠየቅ የሚገባህ ከውጪ አገር ተወላጅ እንጂ ከእስራኤላዊ ወገንህ አይደለም፤ ይህን ሕግ ፈጽም፤ እግዚአብሔር አምላክህም ሄደህ በምትወርሳት ምድር የምትሠራውን ሁሉ ይባርክልሃል።


ምቹ ጊዜ ካገኘን ለሰዎች ሁሉ ይልቁንም ለሚያምኑ ቤተ ሰዎች መልካም ነገርን እናድርግ።


ባሪያ ሁልጊዜ በቤት ውስጥ አይኖርም፤ ልጅ ግን ሁልጊዜ በቤት ውስጥ ይኖራል።


“በድኽነት ከሚኖሩት ሕዝቤ መካከል ለአንዱ እንኳ ገንዘብ ብታበድር፥ እንደ ገንዘብ አበዳሪ በመሆን ወለድ ጨምሮ እንዲከፍልህ አትጠይቀው።


አፈጻጸሙም እንደሚከተለው ነው፤ ለእስራኤላዊ ወገኑ ገንዘብ ያበደረ ሁሉ ያበደረውን ብድር ይሰርዝለት፤ እግዚአብሔር የዕዳ መሰረዣ ዓመት ነው ብሎ ያወጀበት ዓመት ስለ ሆነ ከእስራኤላዊ ወገኑ ያበደረውን ገንዘብ ለመቀበል አይፈልግ።


“ለእግዚአብሔር አምላክህ ስእለት በምታደርግበት ጊዜ ለመስጠት ወይም ለመፈጸም ቃል የገባህበትን ስእለት አታዘግይ፤ እግዚአብሔር አንተ የገባኸውን ቃል እንድትፈጽም ይፈልጋል፤ ስእለትህን ካልፈጸምክ ግን ኃጢአት ይሆንብሃል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements