Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዳንኤል 6:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከዚህ በኋላ አገረ ገዢዎቹና ባለሥልጣኖቹ በማደም ወደ ንጉሡ ሄደው እንዲህ አሉት፦ “ንጉሥ ዳርዮስ ሆይ! አንተ ለዘለዓለም ኑር!

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከዚያም የበላይ አስተዳዳሪዎቹና መሳፍንቱ በአንድነት ወደ ንጉሡ ሄደው እንዲህ አሉ፤ “ንጉሥ ዳርዮስ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ!

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የዚያን ጊዜም አለቆቹና መሳፍንቱ ወደ ንጉሡ ተሰብስበው እንዲህ አሉት፦ ንጉሥ ዳርዮስ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ።

See the chapter Copy




ዳንኤል 6:6
13 Cross References  

እነርሱም “ንጉሡ ለዘለዓለም ይኑር! ሕልምህ ምን እንደ ሆነ ንገረንና ትርጒሙን እናስረዳሃለን” ሲሉ በሶርያ ቋንቋ መለሱለት።


ዳንኤልም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ንጉሥ ሆይ! ለዘለዓለም ኑር!


“ንጉሠ ነገሥቱ ለዘለዓለም ይኑር! የቀድሞ አባቶቼ የተቀበሩባት ከተማ ፍርስራሽ ሆና ስትቀርና የቅጽሮችዋም በሮች በእሳት ሲወድሙ እንዴት አላዝንም?” ስል መለስኩለት።


ቀድሞ ንግሥት የነበረችው የንጉሡ እናት የንጉሡንና የመኳንንቱን ሁካታ ሰምታ ወደ ግብዣው አዳራሽ በመግባት እንዲህ አለች፦ “ንጉሥ ሆይ! ለዘለዓለም ኑር! በዚህ ጉዳይ ይህን ያኽል ልትጨነቅና ፊትህም ሊገረጣ አይገባም፤


ጳውሎስ ተጠርቶ በመጣ ጊዜ፥ ጠርጠሉስ እንዲህ ሲል ክሱን ጀመረ፤ “ክቡር ፊልክስ ሆይ! በአንተ አማካይነት ብዙ ሰላም አግኝተናል፤ በመልካም አስተዳደርህም ለሕዝባችን መሻሻል ተገኝቶአል፤


እነዚህም ዐድመኞች በአንድነት ሄደው፥ ዳንኤል ወደ ፈጣሪው ሲጸልይና ሲለምን አገኙት።


ንጉሡን ናቡከደነፆርንም እንዲህ አሉት፦ “ንጉሥ ሆይ! ለዘለዓለም ኑር!


እንደ አረጀ ግድግዳና እንደ ተነቃነቀ አጥር ዐቅም ያነሰውን ሰው፥ ሁላችሁም በእርሱ ላይ አደጋ እየጣላችሁ። እስከ መቼ ስታጠቁት ትኖራላችሁ?


ተሰባስበው ይሸምቁብኛል፤ እርምጃዬን ሁሉ ይከታተላሉ፤ ሕይወቴንም ለማጥፋት ያደባሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements