| ዳንኤል 2:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም49 በዳንኤልም አሳሳቢነት ንጉሡ ሲድራቅን፥ ሚሳቅንና አብደናጎን በባቢሎን አውራጃዎች ሁሉ ላይ ገዢዎች አድርጎ ሾማቸው፤ ዳንኤል ግን ከንጉሡ አደባባይ ሳይለይ ኖረ።See the chapter አዲሱ መደበኛ ትርጒም49 ከዚህም በላይ በዳንኤል አሳሳቢነት ንጉሡ ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብደናጎን የባቢሎን አውራጃ አስተዳዳሪዎች አድርጎ ሾማቸው፤ ዳንኤል ግን በቤተ መንግሥት ተቀመጠ።See the chapter መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)49 ዳንኤልም ንጉሡን ለመነ፥ እርሱም ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎምን በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ ሾማቸው፥ ዳንኤል ግን በንጉሡ በር ነበረ።See the chapter |