Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዳንኤል 11:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 “የሶርያ ንጉሥ መላ ሠራዊቱን ሰብስቦ ለመዝመት ያቅዳል፤ የጠላትን መንግሥት ለመደምሰስ ሴት ልጁን በመዳር ከጠላት ንጉሥ ጋር የትብብር ስምምነት ይዋዋላል፤ ይሁን እንጂ ዕቅዱ አይሳካለትም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 በመንግሥቱ ያለውን ሰራዊት ሁሉ ይዞ ለመምጣት ይወስናል፤ ከደቡብም ንጉሥ ጋራ ይስማማል፤ ይህንም መንግሥት ለመጣል ሴት ልጁን ይድርለታል፤ ይሁን እንጂ ዕቅዱ አይሳካለትም፤ ያሰበውም ነገር አይጠቅመውም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከመንግሥቱም ሁሉ ኃይል ጋር ይመጣ ዘንድ ፊቱን ያቀናል፥ ከእርሱም ጋር አንድነትን ያደርጋል፥ ያረክሳትም ዘንድ ሴትን ልጅ ይሰጠዋል፥ እርስዋም አትጸናም ለእርሱም አትሆንም።

See the chapter Copy




ዳንኤል 11:17
15 Cross References  

“ወደ ኢየሩሳሌም ከበባ ትኲር ብለህ ተመልከት፤ እጅህንም አንሥተህ የማስጠንቀቂያ ትንቢት በእርስዋ ላይ ተናገር።


የብረት ምጣድም ወስደህ በአንተና በከተማይቱ መካከል እንደ ቅጽር አቁመው፤ ፊትህንም ወደ ከተማይቱ አቅና፤ የተከበበችም ትምሰል፤ የምትከባትም አንተው ነህ፤ ይህም ለእስራኤል ሕዝብ ምልክት ይሆናል።


በዚያን ጊዜ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል በጋት ከተማ ላይ አደጋ ጥሎ ያዛት፤ ቀጥሎም በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል ወሰነ።


እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል?


“ከእኔ ጋር ያልሆነ ሁሉ እኔን ይቃወማል፤ ከእኔም ጋር የማይሰበስብ ይበትናል።


ኢየሱስ የሚያርግበት ቀን በተቃረበ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቈርጦ ተነሣ።


ከእኔ ጋር ያልሆነ ሁሉ ተቃዋሚዬ ነው፤ ከእኔም ጋር የማይሰበስብ ይበትናል።


ከዚያ በኋላ ንጉሡ ወደ ገዛ አገሩ ምሽጎች ይመለሳል፤ ነገር ግን ተሰናክሎ ስለሚወድቅ ዳግመኛ አይታይም።


ከስድሳ ሁለት ሳምንት በኋላ መሲሑ ያለ ፍትሕ ይገደላል፤ የሚገደለውም ለራሱ አይደለም፤ የሚመጣው መሪ ወታደሮች ቤተ መቅደሱንና ከተማይቱን ይደመስሳሉ፤ መጨረሻውም እንደ ጐርፍ ይመጣል፤ ውድመት ስለ ታወጀ ጦርነት እስከ መጨረሻ ይቀጥላል።


“የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን ወደ ዐሞን ምድር አዙረህ በዐሞናውያን ላይ ትንቢት ተናገር።


ባቢሎናውያን ብዙ ሰዎችን ለመግደል ቦይ ቆፍረው ዐፈር በመደልደል ምሽግ በሚሠሩበት ጊዜ፥ የግብጽ ንጉሥ ብዙ ተዋጊና ብርቱ ሠራዊት እንኳ መጥቶ በመዋጋት ሊረዳው አይችልም።


ሰዎች ብዙ ነገር ያቅዳሉ፤ ተፈጻሚነትን የሚያገኘው ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።


እኔ ወደ አንተ በምጣራበት ቀን፥ ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር መሆኑንም በዚህ ዐውቃለሁ።


ኢዮሣፍጥ እጅግ ስለ ፈራ ፈቃዱን እንዲገልጥለት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ከዚህ በኋላ በመላው አገሪቱ ሕዝቡ ሁሉ እንዲጾም ትእዛዝ አስተላለፈ፤


“ሠራዊታቸው ሁሉ የዐመፅ ሥራ ለመፈጸም ይገሠግሣሉ፤ ፊታቸው ከወደ ምሥራቅ እንደሚመጣ ነፋስ ያቃጥላል፤ ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements